ለፊዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአመራር አካላት በአስተሳሰብ/አመለካከት ግንባታ (Mind set) በአመራርነት ክህሎት (Leader ship) ፣ በስሜት ብልህነት( Emotional Intelligence) እና በሌሎች ተዛማጅ የአመራርነትና የአእምሮ ማበልጸጊያ ይዘቶች ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ የስልጠናውን መርሀ ግብር ሲከፍቱ ባደረጉት አጭር ንግግር ስልጠናው የመ/ቤቱን አመራሮች የአመራርነት እና የአስተሳሰብ ክህሎት የበለጠ ለማጎልበት የተዘጋጀ በመሆኑ በርካታ ዕውቀትና ክህሎት የሚገኝበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸው ወደፊት በሚዘጋጁ መርሀ ግብሮች ለሌሎች የመ/ቤቱ ሠራተኞችም ተመሳሳይ የአእምሮ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ይሰጣሉ ብለዋል፡፡
ከታህሳስ 14-19 /2015 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራር አካላት የሚሳተፉ ሲሆን የስልጠናው ትኩረት የመሪዎች ራዕይ (Vision for Leaders)፣ ራስን መቆጣጠር( Self-Management)፣ የአነጋገር ክህሎት( Speaking skill) ፣የመሪዎች ባህሪያት (Leaders Traits) እና የስጋት ስራ አመራር( Risk Management) በሚሉና በሌሎች ተያያዥ ይዘቶች ዙሪያ እንደሚሆን ታውቋል፡፡