የአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስር የሚገኘው የአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE- Center of Audit Excellency) የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ሥራን በተለያየ አግባብ ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሥልጠናዎች ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም መስጠት የጀመረ ሲሆን ስልጠናው እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
በነዚህ የሥልጠና ቀናት በክዋኔ ኦዲት፣ በውስጥ ቁጥጥር ኦዲት፣ በመልዕክት ቀረጻና ሪፖርት አጻጻፍ እንዲሁም የኦዲት ቡድንን በማደራጀትና በመመምራት ዙሪያ ግንዛቤ የማሳደግ ሥራዎች እንደሚሠሩ ተጠቁሟል፡፡
በመጀመሪያ ዙር ስልጠናም 35 የዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ከአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE- Center of Audit Excellency) ከመጡ ልዑካን ጋር ጥቅምት 08 ቀን 2015 ዓ.ም ለመ/ቤቱ በሚያደርጉት የአቅም ግንባታ ድጋፍ ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል፡፡





