News

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከአሜሪካው የኦዲት ልህቀት ማዕከል( CAE- Center of Audit Excellency) ልዑካን ጋር ውይይት አደረገ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ከአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል( CAE- Center of Audit Excellency) ልዑካን ጋር ማዕከሉ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ( USAID) በኩል የኦዲት ተግባራትን ለማጎልበት እየተሰጠ ባለው የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሁኔታ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

የአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE) በአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስር በመሆን የኦዲት ተግባራትን በአቅም ግንባታና ልምዶችን በማካፈል ድጋፍ እያደረገ ያለ ተቋም ነው፡፡

ከማዕከሉ ልዑካን ጋር ውይይት ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የተለያዩ የኦዲት ተግባራትን ለማጠናከር በማዕከሉ በኩል ለመ/ቤቱ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸው በውይይቱ ላይ ድጋፉ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ጠቃሚ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡

የማዕከሉ የአቅም ግንባታ ድጋፍ አካል በሆነው የስልጠና መርሀ ግብር መሰረትም በክዋኔ ኦዲት፣ በውስጥ ቁጥጥር ኦዲት፣ በመልዕክት ቀረጻና የሪፖርት አጻጻፍ እንዲሁም የኦዲት ቡድንን በማደራጀትና በመመምራት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ከመጪው ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጡ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

በውይይቱ መጨረሻም የልዑካን ቡድኑ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠቃሚ ልምዶችን ለመቅሰም ያስችለዋል ያላቸውንና የአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሚጠቀምባቸውን “Standards for Internal Control in the Federal Government” የሚል አረንገዴ መጽሀፍ (Green Book) እና “Government Auditing Standards” የሚል ቢጫ መጽሀፍ (Yellow Book) ለመ/ቤቱ አበርክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *