News

የተቋማቱ ሠራተኞች ቅጥር ግቢያቸውና አካባቢያቸውን አፀዱ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከብሮድካስት ባለሥልጣን መ/ቤቶች ጋር በመሆን የጋራ ቅጥር ግቢያቸውንና በግቢው አከባቢ የሚገኘውን ሥፍራ የካቲት 16፣ 2010 ዓ.ም አፀዱ፡፡

በፅዳት ስነ-ሥርዓቱ  የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃለፊዎችና ሠራተኞች የተሣተፉ ሲሆን ክቡር ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሠራተኛው በራስ ተነሳሽነት ያደረገውን የፅዳት ተሳትፎ አድንቀው በቀጣይም ተከታታይነት ባለው መልኩ ሠራተኛው የሥራ አካባቢውን በማፅዳት ምቹ የሥራ ቦታ መፍጠር እንደሚጠበቅበት ገልፀዋል፡፡

የሦስቱ ተቋማት የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አወቀ አግዘው እንደገለፁት የፅዳት ስነ-ሥርዓቱን በየወሩ ለማከናወን መታቀዱን ገልፀው በቀጣይም ምቹ የሥራ ቦታ ለመፍጠር ሁሉንም ሠራተኛ ባሳተፈ ሁኔታ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በፅዳት ስነ-ሥርዓቱ ሠራተኞች በንቃት የተሳተፉ ሲሆን ንፁህ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር የተጀመረው ተግባር ያለማቋረጥ ሊተገበር እንደሚገባ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *