News

ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግር ስራዎች ፈጠራንና ፍጥነትን ትኩረት አድርገው እንዲከናወኑ ተጠየቀ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ምርምር እና የዕውቀት ሽግግር ውጤታማነት ላይ ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት የታዩ ግኝቶች ላይ በተደረገ ውይይት የዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዎች በተያዘላቸው በጀት፣ በተወሰነላቸው ጊዜና ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ በአግባቡ መፍጠንና መተግበር እንዳለባቸው ተጠየቀ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የኦዲት ባለድርሻ አካላት ሕዳር 15/ 2018 ዓ.ም  ባካሄዱት ይፋዊ ውይይት  በዩኒቨርሲቲው ለምርምር የሚፈሰው የአገር ሃብት በርካታ ቢሆንም ሀብቱ እንዳይባክንና በአግባቡ እንዲያዝ ለምርምር የተመደበለትን ገንዘብ በአግባቡ እና ሙሉ በሙሉ ለምርምር ተግባር መዋሉን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ያልተዘረጋ ከመሆኑ ባለፈ የምርምር ፈንድ አስተዳደርና አጠቃቀም መመሪያ ያልተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል።

የኦዲት ግኝቶችን ለማሻሻል በዩኒቨርሲቲው የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲብራሩ ከቋሚ ኮሚቴው ተጠይቆ በመድረኩ የተገኙ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ግብረ ምልሶቹን ተከትሎ ከቋሚ ኮሚቴ አባላትና ባለድርሻ አካላት ገንቢ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክዋኔ ኦዲት ላይ የቀረበው ሪፖርት የሚሸፍነው  ከ2012 እስከ 2017 የነበረውን መሆኑን ገልፀው የዩኒቨርሲቲውን የቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግር በተመለከተ የተደረገው ኦዲት  26 የመመዘኛ መስፈርቶችና ሶስት የትኩረት አቅጣጫዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ክብርት ወ/ሮ መሰረት ማብራሪያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተካሄደው ኦዲት ያስቀመጣቸው ሶስት የትኩረት አቅጣጫዎች የዩኒቨርሲቲውን የምርምር ፈንድ አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት ኢኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ፣ በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ የምርምር ስራዎች ግብዓት ግዥ ስርኣት ኢኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ማየት፣ በዩኒቨርሲቲው የተቀናጀ መረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርዓት ቀልጣፋና በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ መሆኑን የሚሉት ይገኙበታል።

ክብርት ዋና ኦዲተሯ አስከትለውም የዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዎች ለታለመላቸው ዓላማ፣ በተያዘላቸው በጀት፣ በተወሰነላቸው የጊዜ ሰሌዳ ፈጠራና ፍጥነትን ባማከለ ሁኔታ በአግባቡ እንዲተግበሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክዋኔ ኦዲት ዘርፍ ም/ዋና ኦዲተር አቶ ሃጂ ኢብሳ በበኩላቸው የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሰረት የፋይናንሻል፣ የህጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት እንደሚያደርግ ጠቅሰው ለምርምር የተመደበን በጀት አጠቃቀም፣ በወጪ አስተዳደር ዙሪያ፣ ስለፕሮጀክቶች መዘግየት እና ሌሎች ወሳኝና ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይም  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የክዋኔ ኦዲት ዘርፍ ንዑስ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሱመያ ደሳለው በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በተለይም ከክዋኔ ኦዲት ግኝቶች በኋላ ተቋሙ ለመስራት የሄደበትን ርቀት ያነሱ ሲሆን በዚህም መመሪያ የሌለውን እንዲኖረው ከማድረግ ፣ የቀሩ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ፣ የአስተዳደር ስርዓቶችን ከማስተካከል  እንዲሁም በግኝቶች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ከመስራት አንፃር የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን ጠቅሰዋል። በቀጣይ ባልተከናወኑ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ ከኦዲት ባለድርሻ አካላት በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ በቀጣይ የታዩ ክፍተቶችን ከማስተካከል ባለፈ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግር ስራዎች ውጤታማነት ላይ ዩኒቨርሲቲው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

Auditor General Calls for Greater Efficiency and Innovation in ASTU’s Research Activities

The OFAG has urged Adama Science and Technology University to significantly enhance the efficiency, innovation, and timeliness of its research and knowledge transfer programs.

The call followed a performance audit evaluating how effectively the university manages technological research and disseminates scientific knowledge.

During a public hearing convened by the Standing Committee on Government Expenditure Management and Control, senior leaders, including University President (PhD), were asked to outline the corrective actions taken in response to earlier audit findings.

Members of the Standing Committee expressed concern that, despite receiving substantial public funding, ASTU still lacks a robust system to oversee the proper utilization of research budgets. They also questioned whether the University had made progress in preparing the essential guidelines for managing research funds that were missing at the time of the audit.

Auditor General reported that the audit, covering the period from 2020 to 2024, assessed ASTU’s performance using 26 criteria across three key areas: research fund management, the effectiveness

of research activities, and the efficiency of information management systems.

She urged the university to ensure that research activities are completed within budget, delivered on schedule, and executed with greater creativity and innovation.

Deputy Auditor General raised persistent concerns regarding the university’s budget utilization and

expenditure control. He also highlighted repeated delays in research projects that require urgent attention.

Hon. Mrs. Chairperson for the Performance Audit subcommittee of the PAC, acknowledged

progress in drafting guidelines, completing outstanding projects, and improving management systems. However, she emphasized that remaining weaknesses must be addressed urgently.

Responding to the comments, President Lami Guta (PhD) reaffirmed ASTU’s commitment to strengthening its technological research and knowledge transfer efforts while working to resolve the identified gaps.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *