የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ጨምሮ ከሌሎች የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) የተውጣጡ የኦዲት ኤክስፐርቶች የተሳተፉበት አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡
በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አስተባባሪነት የተካሄደው አውደ ጥናት በዋናነት ግሎባል ፈንድ (Global Fund)፣ የክትባት ትብብር (Vaccine Alliance-Gavi) እና አፍሮ ሳይ -ኢ(AFROSAI-E) ባላቸው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት መሠረት የጤናውን ዘርፍ በማገዝ በተለይም የኤች አይቨ. ኤድስ፣ የሳንባ በሽታ እና ወባን ለመከላከል እና የሰዎችን በሽታን የመቋቋም ኃይል ለማጠናከር የሚተገበሩ ስራዎችን ለማገዝ የትብብሩ አለም አቀፍ አካላት ለማህበሩ አባል ሀገራት የሚያደርጉት ድጋፍ በአግባቡ በስራ ላይ መዋሉን ለመቆጣጠር የሚያስችል ውጤታማ ኦዲት ለማድረግ የሚረዳ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከነሀሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አስከ ነሀሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደውን አውደ ጥናት በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሲሆኑ የአለም አቀፍ ትብብሩ ለማህበሩ አባል ሀገራት በጤናው ዘርፍ የሚያደርጋቸው ድጋፎች በበጀት ድጋፍነት ብቻ የሚታዩ ሳይሆኑ የህይወት አድን መሳሪያዎችም ናቸው ብለዋል፡፡
የማህበሩ አባል ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት ሚናና ኃላፊነት የፋይናንሽያል ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ የዘለለ መሆኑን በንግግራቸው የጠቀሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ትብብሮች የሚከናወኑ ትልልቅ ፕሮግራሞች ላይ የሚውሉ ፈንዶች በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥና ተጠያቂነትን ማስፈንም የኦዲት ተቋማት ቀዳሚ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
አውደ ጥናቱ ቀድሞ የነበረውን የተግባራዊ ኦዲት መመሪያዎችን እውቀት የሚጨምር እና ልምዶችን ለመጋራት የሚረዳ አሠራርን የሚያመቻች እንዲሁም በኦዲት ስራ ላይ የሚያጋጥሙ የጋራ ስጋቶችን ለመለየት እና የኦዲት ክትትልና የሪፖርት ስርዓት ስትራቴጂዎችን ለማጎልበት የሚያግዝ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የኦዲቱን ስራ ከግሎባል ፈንድና ከቫክሲን አሊያንስ (Gavi) በአፈጻጸም ላይ የተመሰረተ ፈንዲንግ ሞዴል አሠራር ጋር ለማጣጣም እና በአሠራር ላይ ህጋዊነትን፣ ግልጽነትንና ቀጣይነትን ለማረጋገጥም የአውደ ጥናቱ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አክለውም የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በቆይታቸው ርዕሰ ጉዳዩን በሚመለከት በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ ያሏቸውን የተለያዩ ተሞክሮዎችና ልምዶች እንዲጋሩ በመክፈቻ ንግግራው ያሳሰቡት ክብርት ወ/ሮ መሠረት በፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ላይ የሚውለው እያንዳንዱ ሀብት አፈጻጸም ላይ ሊኖር የሚገባውን እሴት የሚያሳድግ የታማኝነት፣ የተጠያቂነት እና ቀጣይነት ያለው የመሻሻል ባህል እንዲጎለብት የማህበሩ የዋና ኦዲተር ተቋማት የጋራ ጥረት ተገቢ መሆንኑን ለተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም አጋር የሆኑት ግሎባል ፈንድና ቫክሲን አሊያንስ እያደረጉ ላሉት ድጋፍ እንዲሁም አውደ ጥናቱን በማመቻቸት ለተሳተፉ አካላትና ለመላው ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አክለውም ተሳታፊዎች በአውደ ጥናቱ በሚያገኙት ጊዜና አጋጣሚ በአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉና ከተማዋን ከማስዋብና የኢኮኖሚ ምንጭ ከመሆን ባሻገር ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉትን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንዲጎበኙ በጋበዙት መሠረት ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የሚገኝ አንድ በግሎባል ፈንድ የሚደገፍ የጤና ጣቢያን እንቅሰቀሴን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
AFROSAI-E Audit Experts to Strengthen Oversight on Funds of Global Health
Audit experts from different countries under the African Organization of Supreme Audit Institutions-English Speaking – AFROSAI-E gathered in Addis Ababa for a five-day workshop aimed at strengthening oversight of global funds allocated to health programs in Ethiopia.
The workshop discussions focused on improving audit practices for resources dedicated to fighting AIDS, Tuberculosis, Malaria, and supporting immunization initiatives.
Opening the workshop, H.E. Mrs. Meseret Damtie the Auditor General, OFAG Ethiopia emphasized that public audit work must go beyond financial investigations to ensure programmatic accountability—making sure funds truly deliver health outcomes for communities.
She finally expressed warm gratitude to partners like the Global Fund and GAVI for their continued support, and to AFROSAI-E for its commitment to advancing the role of Supreme Audit Institutions.
The workshop, organized by AFROSAI-E and hosted by the Ethiopian Office of the Federal Auditor General, also facilitated opportunity to the participants in order to visit and experience the performance and effectiveness of one of the health centers funded by the Global Fund and other development projects in Addis Ababa.