News

የ23ኛው የፌዴራል፣ የክልልና የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና የኦዲት የባለድርሻ አካላት አመታዊ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር እና በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ በአውሮጳ ህብረት ድጋፍ የተካሄደው የ23ኛው የፌዴራል፣ የክልልና የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና የኦዲት የባለድርሻ አካላት አመታዊ መደበኛ ጉባኤ መድረክ  በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የመክፈቻ ንግግሮች በይፋ ከተከፈተ በኋላ በተለያዩ የጉባኤው አጀንዳዎች ላይ በመምከር እና ቀጣይ ስራዎች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ  በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በየደረጃው የሚገኙ የኦዲት ተቋማት የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እንዲሁም የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር ለማጎልበት ቀዳሚና ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

የኦዲት ተቋማት ተአማኒነትና የአሠራር ነጻነት አስፈላጊ መሆኑን ጨምረው የጠቀሱት የተከበሩ ም/አፈ-ጉባኤዋ በህገ መንግስቱና በየደረጃው በአዋጅ በተሰጧቸው አዋጆች መሠረት ተጨባጭ የሆኑ የኦዲት ተግባራትን በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ እና ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በበኩሉ በውጭና የሀገር ውስጥ ልምዶቹና ተሞክሮዎቹ ለክልልና ለከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያጠናክርና የክልልና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ከመ/ቤቱ ጋር እያደረጉ ያሉትን የስራ መስተጋብርና ትብብር እንዲያጠናክሩ ጨምረው ያሳሰቡት አፈ ጉባኤዋ የኢ.ፌ.ዲ ሪ. የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም ሆነ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም በየደረጃው የሚገኙ የኦዲት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እያደረጉ ያሉትን ተጨባጭ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የመደገፍ ስራቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

23ኛውን ጉባኤ በደመቀ ሁኔታ ላዘጋጁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤትና የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት  የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በበኩላቸው የሀገርንና የህዝብን ውስን ሀብት በብልሹ አሠራር የማባከን ተግዳሮቶች ለመታደግ በየደረጃው ያሉ የዋና ኦዲተር ተቋማትና የፌዴራልና የክልል ም/ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እያከናወኑ ያሉት ተግባር ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፌዴራልና የክልል እንዲሁም የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከርና በየደረጃው ያሉ የኦዲት ተቋማትን አቅም ለማሳደግ ጉባኤው በ1989 ዓ.ም እንዲመሰረት ግንባር ቀደም ሚና ከመጫወት ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ መ/ቤቱ ይህንኑ የሀገሪቱን የኦዲት ስራ በሁለንተናዊ መልኩ የማጠናከር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የክልል እና የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች እና በየደረጃው ያሉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤቶችና ባለድርሻ አካላትም ለቅንጅታዊ አሠራሩ ያላቸውን ተነሳሽነትና እያበረከቱ ያሉትን አስተዋጽኦ በንግግራቸው የጠቀሱት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ 23ኛው የፌዴራል፣ የክልልና የከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና ባለድርሻ አካላት አመታዊ ጉባኤ የሚወያይባቸውን መሠረታዊ ጉዳዮችና አጀንዳዎች በንግግራቸው በዝርዝር በማቅረብ ጉባኤው እንዲጀመር አድርገዋል፡፡

ጉባኤው በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በኩል የቀረቡ የውይይት አጀንዳዎችን ያጸደቀ ሲሆን በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም በተካሄደው 22ኛው መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና የተሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት አስመልክቶ ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የእቅድና በጀት ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ደቦጭ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

ከ22ኛው ጉባኤ በኋላ በየደረጃው የሚገኙ የኦዲት ተቋማት በነጠላ ኦዲት አተገባበር፣ በኦዲት ሽፋን፣ በኦዲት ጥራት፤ በኦዲት ግኝት እርምጃ አወሳሰድ፤ ተጠያቂነት በማረጋገጥ የባለድርሻ አካላትን አቅም በማሳደግ እና የውስጥ ኦዲትን በማጠናከር ረገድ የተሻሻሉ ለውጦች የታዩባቸው ተግባራት መከናወናቸው በዝርዝር በቀረበው ሪፖርት የተገለፀ ሲሆን እርምጃ ከመውሰድ አንጻር ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ያለው ስራ ተጨማሪ ጥረትን የሚጠይቅ መሆኑም ተመላክቷል።  ከገለጻው በኋላም በአፈጻጸም ሂደቱ ላይ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የተመራ ዝርዝር ውይይትና ግምገማ ጉባኤውን ባሳተፈ መልኩ  ተካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ መድረክ በነጠላ ኦዲት አተገባበር ላይ የኦዲት ጥራት ማረጋገጥን በተመለከተ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሰዋሊህ ግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን አቅም በመገንባት ረገድ ለሀገራዊና ቀጠናዊ አልፎም ለአህጉራዊ የኦዲት ስራ መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ታስቦ ከ22ኛው ጉባኤ ጀምሮ  የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑለት የሚገኘው ሀገር አቀፍ የኦዲት ስልጠና ማዕከል  የቦታ መረጣና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት ጥናት ሲያደርግ የቆየው ኮሚቴ አፈጻጸም ሪፖርት በኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አመንቴ መቻሉ ቀርቦ በጉባኤው ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጥናቱን መሠረት ባደረገ መልኩ ማዕከሉ የሚገነባበትን ቦታ ጉባኤው ወስኗል፡፡

በዚህ የ23ኛው የፌዴራል፣ የክልልና የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና የኦዲት የባለድርሻ አካላት አመታዊ መደበኛ ጉባኤ በቀጣይ በጉባኤው አባላት በተናጠልና በጋራ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ዝርዝር የስራ ክፍፍልን መሠረት ያደረጉ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን የጉባኤውን አጀንዳዎች ተከትሎ ከተሳታፊዎች የተነሱ አስተያየቶችን መሠረት ያደረጉ የማጠቃለያ ሀሳቦችና ማብራሪያዎች በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤና ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሰ ቀርበው ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

Nationwide Annual Auditing Conferences for better audit Performance

 * The joint work group of the Office of the Federal Auditor General, Offices of the Regional & Federal Cities Administration Auditor General, and the Audit Stakeholders conducted the 23rd regular annual conference, and put forward fundamental directions and activities to be carried out in the next one year group engagements of auditing practices.

The 23rd Federal, Regional and Federal cities administration Supreme Audit Institutions and other audit stakeholders’ annual conference, sponsored by the European Union (EU), made effective & profitable discussions on the group common agenda of nationwide auditing issues.

In the meeting, held from June 4-6 3/2025 in Arbaminch, South Ethiopia Regional State; the Honorable guest, H.E Mrs.Lomi Bedio, Deputy House Speaker of the Ethiopian House of People’s Representatives, H.E Alemayehu Bewdi, Speaker of the House of the South Ethiopian Regional State, and H.E Mrs. Meseret Damte, the Auditor General of the Office of the Federal Auditor General-OFAG made opening speeches by confirming significant roles and advantages of the regular annual conferences for the growth of nationwide auditing sector.

H.E Mrs. Meseret Damtie, the Auditor General, SAI Ethiopia particularly remarked the meeting specific agendas and contents in her part of speech by noticing the gathering particular responsibilities and  duties of each group members shared and given in the last 22nd annual conference to be carried out in the last budget year.

By mentioning unique, shared and common contributions and encouraging roles of the Office of the Federal Auditor General, other regional audit institutions and key audit stakeholders including houses of people’s representatives at different levels for tangible progress of auditing tasks; H.E Mrs. Meseret Damtie added her propositions that the gathering should have further workable commitment for more nationwide auditing successes.

In such 23rd annual meeting of the group, the gathering made fruitful discussions on the effectiveness of the group joint work accomplishments by specifying the strengths, weaknesses, drawbacks, and finally proposed possible solutions that add values on the group efforts.

At the final session of the conference, the group put forward proper resolutions and directions to be practical in the next group endeavors.

 

   

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *