በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራና ም/ኮሚሽነር ጀነራሎችን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች የተካተቱበት የፌዴራል ፖሊስ የአመራር ቡድን መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮች በሁለቱ መ/ቤቶች የጋራ የትብብር ሥራዎችን በተመለከተ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የበላይ አመራሮች ጋር የሁለቱን ተቋማት የጋራ ጉዳዮች በሚመለከት ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከውይይታቸው በኋላም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን አሠራርና በአዲስ መልክ ታድሶ በስራ ላይ የዋለውን የመ/ቤቱን ህንጻና የስራ ቢሮዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡