News

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ለአዲሱ የ2018 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለመ/ቤቱ ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለአዲሱ 2018 . በሠላም አደረሰን!

ውድ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለአዲሱ የ2018 ዓ.ም በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የተጠናቀቀው የ2017 ዓ.ም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እንደ ተቋም በኦዲቱም ሆነ በድጋፍ ዘርፎች ዘርፈ ብዙና ውጤታማ የሪፎርም ተግባራትን በማከናወን ተቋማዊ እርምጃን ያሳየ ውጤት ያስመዘገበበት ነው፡፡

በተለይም አመቱ ዋናው የመ/ቤቱ የኦዲት ስራ አፈጻጸም በሽፋንም ሆነ በጥራት መሻሻል የታየበት ከመሆኑም ባሻገር ከክልልና ከተማ አስተዳደር የኦዲት ተቋማት እንዲሁም የውጭ አጋር ተቋማትና አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ ስራ ይበልጥ በማጠናከር ሀገራዊውን የኦዲት ስራ ከነበረበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ጥረት የተደረገበትና በዚህም ስኬታማ አፈጻጸም የታየበት ነው፡፡

የ2017 ዓ.ም እንደ ሀገርም በርካታና ውጤታማ ሀገራዊ ክንውኖች የተተገበሩበት ሲሆን በተለይም ከአመታት በት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ተጀምሮና በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ በአዲሱ የ2018 ዓ.ም ዋዜማ እውን የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድባችን መቋጫውን አግኝቶ ለምረቃ የበቃበት አመት ነው፡፡ በዚህም እንደ ዜጋ እንኮራለን፡፡

በአዲስ የምንቀበለው የ2018 ዓ.ም በእነዚህ ተቋማዊና ሀገራዊ ስኬቶች ላይ ሆነንና ያለንን ተባብሮ የመስራት የቁርጠኝነት እንቅስቃሴና እና በስራ ዲሲፒሊን የተመራ አፈጻጸም የበለጠ በማሳደግ ሌሎች ተጨማሪ ድሎችን የምናስመዘግብበት እንደሚሆን በመተማመን መጪው ዘመን የጤና፣ የሠላም፣ የአብሮነትና እና የተጨማሪ ስኬት እንዲሆን እመኛለሁ!!

መልካም አዲስ አመት!!

መሠረት ዳምጤ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *