News

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራትን ለማሻሻል የበለጠ መስራት እንዳለበት ተገለጸ

የእንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር (አፍሮሳይ-ኢ/ AFROSAI-E) የኦዲተሮች ቡድን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራትን ለማሻሻል የበለጠ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ገለጸ፡፡ ቡድኑ በመ/ቤቱ የኦዲት ጥራት ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቆ ከመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራርና የማኔጅመንት አባላት ጋር የመውጫ ስብሰባ ሚያዝያ 13፣ 2009 ዓ.ም አድርጓል፡፡_DSC0084 improved

የአፍሮሰይ-ኢ የኦዲተሮች ቡድን ሰብሳቢ ሚስ ጆሰፊን ሙኮምባ በመግቢያ ንግግራቸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ሽፋንና ጥራትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነ ቡድኑ መረዳቱን ገልጸውበግምገማው ሂደት የመ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ላሳዩት ቀና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የቡድኑ አባላት ባደረጉት የናሙና ቅኝት/ኦዲት መሰረት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚደረጉት የክዋኔ፣ የፋይናንሻልና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲቶች የጥራት ሁኔታ ላይ የተገኘውን ግኝት አቅርበዋል፡፡

የቡድኑ አባላት በኦዲት ጥራት ላይ ያሉትን ጉድለቶች ያመላከቱ ሲሆን የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ስራን በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም የጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬትን በሰው ኃይልና በቁሳቁስ ለማጠናከር መ/ቤቱ ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲት፣ በውስጥ ግንኙነትና ከባለድርሻ ጋር በሚኖር የቅንጅት ስራ ረገድ መሻሻል ይገባቸዋል ባሉዋቸው ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

በግምገማ ሪፖርቱ ላይ ከመድረኩ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በግምገማ ሪፖርቱ በቀረቡ ግኝቶችና በተያያዥ ጉዳዮች ላይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የተሰጡትን ገንቢ አስተያቶች በመውሰድ መ/ቤቱ በቀጣይ የኦዲት ጥራቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

የአፍሮሰይ-ኢ የኦዲተሮች ቡድን ግምገማ የመጨረሻ ሪፖርት ለአለም ባንክ የሚቀርብ ሲሆን በቀጣይ በ2010 ዓ.ም ተመሳሳይ ግምገማ በመ/ቤቱ ላይ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *