የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከአፍሪካ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ዋና ኦዲተሮች ማህበር (AFROSAI-E) ጋር በመተባበር የአደጋ ጊዜ የኦዲት እቅድ ዝግጅት (DISASTER AUDIT PLANNING) ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡
አውደጥናቱ በአፍሮሳይ-ኢ (AFROSAI-E) ድጋፍ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ዘርፍ የማኔጅመንት አባላት የአደጋ ጊዜ ኦዲት እቅድ ዝግጅት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት የተለያዩ ወረርሽኞች፣ ግጭቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም አሉታዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ምክንያት በየጊዜው የሚከሰቱ አደጋዎች በሕዝብ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ዘላቂ ልማት ላይ ይበልጥ አሳሳቢ አደጋ እየፈጠሩ መጥተዋል ብለዋል።
በተለይም በአፍሪካ ጠንካራ ተቋማት በሌሉበት እና የሀብት ውስንነቶች ይበልጥ ተጋላጭነትን በሚፈጥሩበት አህጉር፣ ውጤታማ የአደጋ እቅድ መተግበሩን ማረጋገጥ ስልታዊ ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ክቡር አቶ አበራ አንስተዋል፡፡
የዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ሚና ከተለምዶዋዊ የፋይናንስ ኦዲት ሥራ ያለፈ መሆኑን ጨምረው የጠቆሙት ም/ዋና ኦዲተሩ፣ የኦዲት ተቋማት የአደጋ ስጋቶችን ለመቆጣጠር የመንግስታትን ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ በመገምገም ሀገራት በቂ ዝግጁነትና ዕቅዶች ያሏቸው መሆኑን፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች በአግባቡ የተዘረጉ እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚመደብ በጀት በግልፅነት እና በውጤታማነት ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥና ስለ አፈጻጸሙም ለዜጎች በግልጽነት እና በነፃነት መረጃ የመስጠት ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
አፍሮሳይ-ኢ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቀጠናው የሚገኙ የዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም በየጊዜው ለማጎልበት የሚያደርገውን ድጋፍ ያደነቁት ም/ዋና ኦዲተሩ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎችም ከዓለም አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ማህበርም (INTOSAI) ሆነ ከቀጠናው የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ጥናቶችን መሠረት አድርገው በመወያየት የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና እውቀትና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ባሳሳቡት መሠረት ተሳታፊዎች በአውደ ጥናቱ ልምድና ተሞክሮ መለዋወጥን መሠረት ያደረገ ቆይታ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
በአውደጥናቱ 25 የሚሆኑ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንሻልና ህጋዊነት ኦዲት፣ የክዋኔ ኦዲት እና እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
Workshop on Disaster Audit Planning to Reinforce Oversight Capacity
The Office of the Federal Auditor General (OFAG), in collaboration with AFROSAI-E, provided a three-day workshop to build auditors’ capacity in planning audits during disasters.
The training focused on challenges such as epidemics, conflicts, climate change, and technological risks—factors that increasingly disrupt public services and development.
Opening the workshop, H.E. Abera Tadesse, Deputy Auditor General of Ethiopia, emphasized that disaster readiness is critical for Africa, where limited resources make countries more vulnerable.
In his remarks, H.E Abera also encouraged auditors to observe beyond finances and ensure governments have effective early warning systems and transparent use of response funds.
AFROSAI-E’s Technical Manager, Mr. Edmond Shoko-Lekhuleni, on the other hand, underlined the need for Supreme Audit Institutions to pay closer attention to disaster-related audits.
The gathering brought together 25 auditors for three days of knowledge and professional skill-sharing and experience exchange.