News

የትግራይ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

የትግራይ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር እና ምክትል ዋና ኦዲተር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም የትግራይ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን መልሶ ለማቋቋም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሊያደርጋቸው በሚችላቸው የአቅም ግንባታ፣ የአሠራር ሥርዓት፣ የግብዓት፣ እና ሌሎች የድጋፍ አይነቶች ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የልዑክ ቡድን አባላት በቀጣይ ወደሥራ ለመግባት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የነበራቸው ጉብኝት፣ የልምድ ልውውጥና ውይይት ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ያገኙበት እንደነበረ ገልጸው ለተደረገላቸው አቀባበል እና እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *