News

የቄራዎች አደረጃጀትና የስጋ ምርት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲጠናከር ተጠየቀ

በግብርናው ዘርፍ የእንሰሳት ቄራዎች አደረጃጀትና የስጋ ምርቶች አገልግሎት አሰጣጥ ኤኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥን ዓላማው አድርጎ በ2015/2016 ኦዲት አመት በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ላይ የተካሄደው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአካባቢ ክዋኔ ኦዲት ያወጣቸውን የአሠራር ክፍተቶች ለማሻሻል የሚያስችል ሥርዓት መጠናከር እንዳለበት ተጠየቀ፡፡

ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተካሄደው ይፋዊ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እንደተገለጸው በህግ ማእቀፍ ዝግጅትና ትግበራ፣ በእንሰሳት ጤንነትና ደህንነት መረጃ አያያዝና ልየታ፣ በቅድመ እርድ ምርመራ ሥርዓት፣ በቄራዎች የኦዲትና የኢንስፔክሽን አሠራር ፣ ለእርድ እንሰሳት በሽታዎች ሊሰጥ በሚገባ ትኩረት፣ ለውጪ ገበያ በሚቀርቡ የእርድ እንሰሳት ጥራትና መጠን፣ በቄራዎች ስታንዳርድ፣አመዘጋገብና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ፣ በቄራዎች ንጽህና አጠባበቅ እና የፍሳሽ ማከሚያ አተገባበር፣ በአካባቢና ማህበረሰብ ተጽእኖ ግምገማ፣ በሠራተኞች ደህንነትና ጥበቃ እና በቅንጅታዊ አሠራር ረገድ መሠረታዊ ክፍተቶች በባለስልጣን መ/ቤቱ አሠራሮች ላይ ታይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማን ጨምሮ በውይይት መድረኩ የተገኙ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ የተነሱትን የኦዲት ግኝቶች አስመልክቶ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ግኝቶቹ ትክክለኛ መሆናቸውንና ከኦዲቱ በኋላ በግኝቶቹ ላይ ኮሚቴ አዋቅሮ ዝርዝር እቅድ በማቀድና በመተግበር በርካታ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ መቻሉንና ቀሪ ክፍተቶችን ለማስተካከልም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከምላሾቹ በኋላ የም/ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ግኝቶቹን ለማስተካከል የሚያስችሉ ጠቃሚ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ግኝቶቹን በመሰረታዊነት ለማሻሻል ያስችላሉ ያሏቸውን አስተያየቶች አቅርበዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ኦዲቱ ከ2013 በጀት አመት ጀምሮ አስከ 2016 የመጀመሪያ አጋማሽ ድረስ ያለውን የባለስልጣን መ/ቤቱን አሠራር በናሙና የዳሰሰ መሆኑንና ትኩረቱም የባለስልጣኑን የእንሰሳት ቄራዎች አደረጃጀትና የስጋ ምርቶች አገልግሎት አሰጣጥ የህግ ማዕቀፍ አተገባበር፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ቅንጅታዊ አሠራር መሠረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አክለውም በግኝቶቹ ላይ የተወሰዱና እየተወሰዱ ያሉ የማሻሻያ እርምጃዎች አበረታች መሆናቸውንና ትግበራቸው በክትትል ኦዲት የሚረጋገጥ መሆኑን ገልጸው በተለይም የህግ ክፍተቶችን ለመድፈን በቅርብ ጸድቆ የወጣው የባለስልጣኑ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች ጸድቀው መተግበር አለባቸው ብለዋል፡፡

ለአለም ገበያ እና ለሀገር ውስጥ የሚሆኑ የስጋና እንስሳ ምርቶችን መለየትና ከገበያ በፊትም የእንስሳቱን ሁኔታ በጥናት ለይቶ መረጃ መያዝ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ አጠቃላይ አሠራሩን ውጤታማ ለማድረግ በባለሀብቱ፣ በባለስልጣን መ/ቤቱንና በተቆጣጣሪ አካላት ጭምር የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመላው ሀገሪቱ ላሉ ቄራዎች የብቃት ማረጋገጫ ከመስጠት በፊት ስታንዳርዱን ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በተጨማሪም ከክልሎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እና የቄራዎችን ስታንዳርድ መጠበቅ እንዲሁም ከቄራዎች የሚወጡ የፍሳሽ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማከም እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ሀገሪቱ ካላት ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ደረጃ አንጻር በዋጋም ሆነ በጥራት ረገድ ያለውን ክፍተት በመቅረፍ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚያስፈልግ ጨምረው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ይህንንም ባለስልጣኑ በጀመረው ሪፎርም ውስጥ ማካተት ይገባዋል ብለዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሴክተሩ ዙሪያ እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችንና አላማዎችን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚገባውና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚያስፈልገው በማጠቃላያ ሀሳባቸው የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በበኩላቸው ቀሪ ክፍተቶችን በሂደት በማስተካከል በየሶስት ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲቀርብ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

 

Abattoirs and Meat Production Delivery Services need to have improved and well working Systems, the Public Hearing claims

The public hearing held on May 26/2015 in the Ethiopian Parliament requested the audit findings discovered in the systems and organizational structure of abattoirs and meat production delivery services under the Ethiopian Agricultural Authority should have been improved to attain effective and efficient meat and animal worldwide market opportunities.

According to the audit findings revealed by the 2023/2024 performance audit of the Office the Federal Auditor General, OFAG, the authority fails to fulfill appropriate and sufficient working systems in the process of organizing slaughterhouses and meat production deliveries due to certain systematical and technical lacks.

Based on the findings discussed in the public hearing, gaps of legal frameworks, lack of organized information on meat animal health care, and also insufficient attention on follow up, auditing and inspection tasks, lack of delivery of quality meat production for export market, absence of fitting structural standards, improper management of waste products, lack of impact assessment on social and environmental surroundings and insufficient joint works are major deficient areas.

Next to suitable corrective suggestions from PAC members, H.E Mrs. Meseret Damtie, the Federal Auditor General, OFAG proposed fundamental observations that help improve the audit findings for better meat production and market accesses.

The auditor General added in her recommendation that implementing suitable legal matters, identifying animals separately to deliver quality meat products for export market, handling and managing enough information, strengthening joint works with other stakeholders, and also proper attention to make changes on perceptions of producers, the authority and regulatory bodies can make the attempts of the authority and the sector more productive and competent.

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *