የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ እና ሌሎች የመ/ቤቱ አመራሮች የተሳተፉበትና በሲሸልስ ዋና ኦዲተር ተቋም (SAI Seychelles) አዘጋጅነት ከግንቦት 11-15/2017 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው 21ኛው የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) ጉባኤ የተለያዩ መርሀ ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል፡፡
ጉባኤው የገቨርኒንግ ቦርድ ልዩ ስብሰባውን ከግንቦት 11-12/2017 ዓ.ም ዋና ኦዲተሮች ብቻ በማሳተፍ ለሁለት ቀናት በዝግ ካካሄደና ጠንካራ አስተያየቶችንና በወደፊት የማህበሩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ግንዛቤዎችን ለመድረኩ ካቀረበ በኋላ ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች የተካፈሉበትን የጋራ ውይይት መድረክ ከግንቦት 13-15/2017 ዓ.ም አካሂዷል፡፡
ጉባኤው በቆይታው የማህበሩን የ2025 ሰትራቴጂክ እቅድ አስመልክቶ ውይይት በማካሄድ የተለያዩ ሀገራት ዋና ኦዲተሮች የማህበሩን አጠቃላይ ውጤታማ አተገባበር እና የአባል ተቋማት አፈጻጸሞችን አስመልክቶ ባቀረቧቸው ማብራሪያና ገለጻዎች ላይ ተወያይቷል፡፡
ከገቨርኒንግ ቦርዱ ዝግ ስብሰባ በኋላ የተካሄደውን የጋራ የውይይት መድረክ የሲሸልስ ም/ፕሬዚዳንት ክቡር ሚ/ር አህመት አፊፍ የከፈቱ ሲሆን የማህበሩ ሰብሳቢ ዋና ኦዲተር ናንሲ ጋቱኑንጉ እና የአዘጋጇ ሀገር ሲሸልስ ዋና ኦዲተር ጃሚኒ ሄራዝ የመክፈቻ ንግግር አድርገው መድረኩ በማህበሩ የ2025 ስትራቴጂክ እቅድ አተገባበር ላይ መክሯል፡፡
ጉባኤው የፓነል ውይይት ያደረገ ሲሆን የተለያዩ የማህበሩ አባል ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የቀጠናዊ ማህበሩን ታሪካዊ ዳራ በማንሳት ከምስረታው ጀምሮ እያሳየ ስላለው እድገትና በተለይም ባለፉት 20 ዓመታት ስላስመዘገበው የስኬት ጉዞ፣ ስለ ማህበሩ የትብብርና የመደጋገፍ ስራዎች እንዲሁም ማህበሩ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት እና ለኦዲት ተግባራት ያበረከተውን አስተዋጽኦ በሚመለከት ለፓናል ውይይት የሚሆን የመድረክ ገለጻዎችን አቅርበዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ እና ሌሎች ዋና ኦዲተሮች በበኩላቸው የከፍተኛ የአመራርነት ልማት መርሀ ግብር ኢኒሼቲቭ ውጤታማነትን መሠረት በማድረግ ይህ የአመራርነት ማጎልበቻ ኢኒሼቲቭ የዋና ኦዲተር ተቋማትን የአዲሱ ትውልድ አስፈጻሚ አመራር ለመቅረጽና ለማጎልበት እያከናወነ ስላለው ጠቃሚ ተግባር የመድረክ ማብራሪያና ገለጻ አቅርበዋል፡፡
በዚህ የማህበሩ 21ኛው ጉባኤ ከ2025 አስከ 2029 የማህበሩ የስትራቴጂክ ምዕራፍ ውስጥ የሚከናወኑ ጉዳዮችም ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመድረኩ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) 23ኛ አመታዊ ጉባኤ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቅርባ ጉባኤውን እንድታዘጋጅ የገቨርኒንግ ቦርዱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የጉባኤው ተጋባዥ የሆኑትን የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ዋና ኦዲተር ጨምሮ ከሌሎች የዋና ኦዲተር ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር የጎንዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
The Auditor General Reflected the Significant Contribution of the AFROSAI-E Leadership Development Initiative
H.E Mrs. Meseret Damtie, the Federal Auditor General, OFAG Ethiopia pointed forward fundamental facts about basic roles of the Leadership Development Program Initiative run by AFROSAI-E (African Organization of English-speaking Supreme Audit Institutions).
In her part of reflection made in the 21st English-speaking subgroup five days summit of AFROSAI-E, held, from May 19-23/2025, in Seychelles, H.E Mrs. Meseret Damtie reflected the benefits of the AFROSAI-E Leadership Development initiative by pointing out practical means that possibly develop the capacity and quality of leadership in Supreme Audit Institutions.
Reflecting focused insights to the gathering by indicating certain practical attempts of AFROSAI-E as well as the initiative, the Auditor General added that the dynamic support of the initiative program can significantly shape the coming generation higher level leadership to become more professional in the auditing areas.
The information from the meeting also indicates that AFROSAI-E accepts the demand of SAI Ethiopia to host the 2027 conference of the Organization.
Moreover, by the side of the meeting, H.E Mrs. Meseret Damtie made profitable discussions with different officials including the Auditor General of SAI United Arab Emirates.
The 21st AFROSAI-E Governing Board Meeting & 2025 Strategic Review hosted by the SAI Seychelles ends May 23, 2025.