News

የማምረቻ ኢንዱስትሪው መሠረታዊ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ተጠየቀ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ  ግሩፕ የፓወር ኢኪዩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የማምረቻ ፋብሪካዎች የስራ አፈጻጸምና የአካባቢ አያያዝና ጥበቃ ሁኔታን ተገቢነት ለማረጋገጥ በ2015/2016 ኦዲት አመት ባካሄደው የክዋኔና የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት መሠረት በማምረቻ ኢንዱስትሪው የማምረቻ ፋብሪካዎች አሠራር ላይ የታዩ ዘርፈ ብዙ መሠረታዊ ችግሮች ተገቢ በሆኑ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲታረሙ ተጠየቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ከሚቴ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ይፋዊ ህዝባዊ ውይይት ኢንዱስትሪው በግዥ አፈጻጸም፣ የማምረቻ ማሽነሪዎችን ጨምሮ በንብረት አጠቃቀምና አያያዝ፣ በገበያ ማፈላለግና በውል ሂደት፣ በአካባቢና ህብረተሰብ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት እና በሠራተኞች አና አካባቢ አያያዝና ደህንነት ዙሪያ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ዋና አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታን ጨምሮ የኢንዱስትሪው የስራ ኃላፊዎች ግኝቶቹን ለማስተካከል በተወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቆ ምላሾቻቸውን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ግኝቶቹ ትክክለኛ መሆናቸውን በመግለጽ እና ችግሮቹ ቀደም ካሉት አመታት ጀምሮ የነበሩና መሠረታዊ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በመጠቆም አበረታች የማሻሻያ እርምጃዎች መወሰዳቸውንና ቀሪዎቹን ችግሮች ለመቅረፍም ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ችግሮቹን በመሠረታዊነትና በሚፈለገው ደረጃ ለማስተካከል የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የተቋማዊ ገንዘብ እጥረትና ከተቋማዊ አቅም ማነስ የመነጨ የባንክ ብድር አለማግኘት እንዲሁም ከሰው ኃይል አቅም ጋር የተያያዙ ክፍተቶች እንቅፋት እንደሆኑባቸው ገልጸዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹን ምላሽ ተከትሎ የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ለችግሮቹ መፍቻ ይሆናሉ ያሏቸውን ሀሳቦችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ያቀረቡ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠ የተሰጡ ምላሾችን መሠረት ያደረጉና ከተቋሙ የግኝት ማሻሻያ የድርጊት መርሀ ግብር አፈጻጸም ጋር የተያያዙ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማስቀደም ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሔ አስተያየቶችን አቅርበዋል፡፡

ኦዲቱ ኢንዱስትሪው በ2022 ዓ.ም አሳካዋለሁ ያለውን ርዕይ ታሳቢ በማድረግ የተካሄደና ከ2013 እስከ 2016 የመጀመሪያ አጋማሽ ድረስ ያሉትን የኢንዱስትሪውን ማምረቻ ፋብሪካዎች አፈጻጸሞች የፈተሸ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር አቶ አበራ ታደሠ በተቋሙ ላይ የተደረጉ የኦዲት ስራዎች በተደጋጋሚና በተለያዩ መንገዶች የተከናውኑ ናቸው ብለዋል፡፡

ኢንዱስትሪው በኦዲቱ ወቅት በተሰጠው የኦዲት ማሻሻያ አስተያየቶች መሠረት የድርጊት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ተግባራዊ ጥረቶች እያደረገ መሆኑ እና በቀጣይ የ2018 በጀት አመት ውጤት ለማምጣት አዲስ እቅድ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ አበረታች መሆኑን በአስተያየቶቻቸው የጠቀሱት ክቡር ም/ዋና ኦዲተሩ በዋናነት በግብአት ግዥና አቅርቦት፣ በምርትና ምርታማነት ሂደት እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃና በሠራተኛ ደህንነት ላይ ያተኮሩ እርምጃዎችን በመውሰድ የአፈጻጸም ችግሮቹን ቀርፎ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

ከፋይናንስ ተቋማትና ከደንበኞች ጋር ያለውን ዘለቄታዊ ግንኙነት በማጠናከር፣ በገበያ ጥናት ላይ በተመሠረት የምርትና የአቅርቦት ሂደት በመመራት፣ ከጥቃቅን ግዥ ይልቅ የማዕከል ግዥን በመተግበር፣ ከህግ ውጪ በሚሠሩ አጥፊዎች ላይ የተጠያቂነት እርምጃን በማጠናከር፣ በውጭ ሀገር ግዥዎች ላይ የዋስትና አሠራርን በመዘርጋት፣ የማምረት አቅምን ለይቶ በጥራት በማምረትና  የሀገር ውስጥም ሆነ የአለም አቀፍ ገበያን ሊስቡ የሚችሉ የምርት መለያ ምልክቶችን በመተግበር እና የአካባቢ ጥበቃና የሠራተኛ ደህንነት ትግበራ ጥራትን በማረጋገጥ ዙሪያ ያሉ አለምአቀፋዊ የጥራት ማረጋገጫ ስርዓቶችን በመተግበር የተሻለ አፈጻጸም ማሳየት ይገባል ብለዋል፡፡

በኦዲቱ ወቅትም ሆነ በመድረኩ የተሰጡ አስተያየቶችን በመውሰድ የኦዲት ግኝቶቹን ለማስተካከል እየተወሰዱ ያሉ አርምጃዎችን ማጠናከር እንደሚገባ በማጠቃለያ አስተያየታቸው ያሳሰቡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተጨባጭ የማሻሻያ ስራዎች ተሰርተው እስከ መጪው ሰኔ 2017 መጨረሻ ድረስ የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲቀርብ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

 

The PAC-Audit Stakeholders Public Hearing Comments the Manufacturing Industry’s Audit Findings

The Public Expenditure Administration and Control Affairs Standing Committee of the Ethiopian Parliament and audit stake holders discussed the audit findings revealed in the product and productivity performance status of the Power Equipment manufacturing Industry of Ethio-Engineering Group.

According to the public hearing held on May 7, 2025, the 2023/2024 performance and environmental protection audit of the Office of the Federal Auditor General-OFAG discovered several & fundamental gaps in the production processes of the industry’s manufacturing plants in different areas.

Based on the points discussed in the public hearing, the industry has been found to be below standard performance in managing, implementing and providing appropriate working systems and inputs in its manufacturing factories.

Illegal procurements, improper management and utilization of machineries and other properties, insufficient and under capacity market practices, unsatisfactory plan accomplishments, inadequate contact with target customers and lack of identifying their market needs, absence of environmental and social impact assessments, and also poor attention to the protection of the environment and workers safety have been major failures of the industry, the audit report confirmed.

After the suitable comments and suggestions of others in the gathering, H.E Ato Abera Tadesse, Deputy Auditor General, the Office of the Federal Auditor General recommended possible solutions and basics that can recover the industry’s working lacks by mentioning fundamental details.

In his workable statements the Deputy Auditor General suggested that the industry should take all the best actions through practical measures of strengthening sustainable interactions with fitting finance entities and customers, practicing market based productivity, implementing concrete accountability, establishing reliable systems on abroad markets, producing quality goods by identifying and considering productive capacity, labeling Products to attract inland and foreign markets, and also by applying worldwide environmental protection and workers safety quality management systems and standards  to achieve effective and efficient productivity.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *