- የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቅርበዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2016 በጀት አመት ያከናወናቸው የተለያዩ የኦዲት ተግባራት አፈጻጸሞች የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመገኘት በንባብ ባቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት ይፋ ሆነዋል፡፡
በዝርዝር በቀረቡት የሂሳብና ህጋዊነት፣ የክዋኔ፣ የልዩ ኦዲትና ሌሎች ኦዲት አፈጻጸሞች መሠረት በበጀት አመቱ ለማከናወን በጥቅሉ ከታቀዱት የሂሳብና ህጋዊነት ኦዲቶች መካከል በወቅታዊ ሁኔታ ከተቋረጡት 6 ኦዲቶች በስተቀር የታቀዱትን በመፈጸም የእቅዱን 96.7 በመቶ ማሳካት መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
ከዚህም ሌላ በበጀት አመቱ 32 አዳዲስ የክዋኔ ኦዲቶች ለማከናወን ታቅዶ 31 እንዲሁም 8 የክትትል ኦዲቶችን በማቀድና 8 በመፈጸም በጥቅሉ 97.5 በመቶ የክዋኔ ኦዲት አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉ በክብርት ዋና ኦዲተሯ ሪፖርት ተመለክቷል፡፡
በተጨማሪም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ተገቢ አካላት ተጠይቀው በመ/ቤቱ የሚካሄዱ የልዩ ኦዲቶችን አፈጻጸም በተመለከተ በበጀት አመቱ 12 ልዩ ኦዲቶችን ለማከናወን ታቅዶ ከተገቢ አካላት ከእቅድ በላይ በርካታ የልዩ ኦዲት ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም 15 ቅድሚያ የሚሰጣቸው ልዩ ኦዲቶችን በማከናወን እና የተጠናቀቁ ኦዲቶችን ሪፖርቶች ጥያቄውን ላቀረቡት አካላት የመላክ ስራ የተሰራ ሲሆን ያልተጠናቀቁ 5 ኦዲቶች በመከናወን ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሪፖርት ከተገለጹና በበጀት አመቱ በኦዲት ተደራጊ ተቋማት አሠራሮች ላይ ከታዩ ግኝቶች መካከል በጥሬ እና በባንክ ገንዘብ አያያዝ፣ በተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች አሠራርና ወቅታዊነት፣ በተመላሽ ሂሳቦች፣ በሰነድና መረጃ አቅርቦት፣ በግንባታ አፈጻጸም ፣ በግብር እና ቀረጥ ህግ አተገባበር፣ በህግ ማዕቀፎች ዝግጅትና አተገባበር፣ በአሠራር ስርዓት፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም እንዲሁም በንብረት አያያዝና አጠቃቀም ረገድ የታዩ ክፍተቶች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የፌዴራል ዋና አዲተር መ/ቤት የበጀት አመቱ አፈጻጸም በሪፖርቱ ተካቶ የቀረበ ሲሆን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የህንጻ እድሳትን በማጠናቀቅ፣ በግብአት መሟላት፣በአቅም ግንባታ ስራዎች፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም የስራ አካባቢን ምቹና ማራኪ በማድረግ ረገድ እና በሌሎች የድጋፍ ዘርፍ ስራዎች የተከናወኑ አፈጻጸሞች ተዘርዝረዋል፡፡
ሪፖርቱ በንባብ ከቀረበ በኋላ ከም/ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በተለይም ኦዲት ተደራጊ ተቋማት በሪፖርቱ ወቅት በም/ቤቱ ያለመገኘታቸው፣ የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ የማይጠቀሙና የበጀት ብክነት የሚያሳዩ ተቋማት መኖራቸው እና ሌሎች በኦዲት ተደራጊ ተቋማት አሠራር ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ከምክር ቤቱ አባላት በተሰጡ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ምላሽ የሚስፈልጋቸው የሪፖርቱን ይዘቶች የሚመለከቱ ጥያቄዎችም ቀርበው በክብርት ዋና ኦዲተሯ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የመ/ቤቱ የኦዲት አፈጻጸም ጠንካራ ጎኖችና መጠናከር ያለባቸው አንኳር ጉዳዮች እንዲሁም የመ/ቤቱን የኦዲት ስራ ለማጠናከርና ለመደገፍ በም/ቤቱ በኩል ሊደረጉ የሚገባቸው ድጋፎችን በሚመለከት በም/ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ከሚቴ ሰበሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር)አስተያየቶች ተሰጥተው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት የማጠቃለያ ሀሳብ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
ሙሉ የሪፖረት አቀራረቡን ሂደት የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማየት ይቻላል
https://www.youtube.com/live/eMCGOXYwE4Y
The Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG) Publicizes the 2023/2024 Budget year Audit Report
- E Mrs. Meseret Damte, the Auditor General, provides the report to the EFDRE House of People’s Representatives.
The Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG) made the 2023/2024 budget year audit report official.
At the congress of the House, held on June 24/2025, the Auditor General H.E Mrs. Meseret Damte, publicized several institutional findings discovered by different audits conducted in the budget year.
According to the entire audit report, the office organized and performed a large number of financial and compliance audits, performance audits, and also special audits.
Detailing the audit outcomes, the Auditor General specified that out of the planned financial and compliance audits of the budget year, the office achieves 96.7%, and also it accomplishes 31 new and 8 follow -up performance audits, which is 97.5 percent of the overall plan.
In the special audits, conducted in the budget year, on the other hand, the office also attains better achievement which is above the plan, the report stated.
In addition to such auditing executions, the report also specifies major institutional plan achievements of the office in its support areas.
Implementation of new technologies, inputs and working systems; accomplishment of the renovation of the office, making of the office working environment attractive and convenient, building institutional capacity and others are foremost successful supporting deeds among the achievements mentioned in the report.
Following the Auditor General report, the congress made constrictive discussion on the details, and suggested that the overall auditing outcomes as well as the endeavors of the office are said to be successful in achieving the plan.
The house members also recommended by mentioning the critical audit findings that serious measures have to be taken on the responsible bodies who abused legal frameworks and working systems in order to ensure accountability.
By Pointing out supportive roll of the facts in the report, the house remarks the audit findings are essential inputs to ensure public accountability, institutional transparency and practice of good governance as well.
Use the video link below for complete reporting process
https://www.youtube.com/live/eMCGOXYwE4Y