Uncategorized

የመ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራርና ሠራተኞች ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር እየተካሄደ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ምክንያት በማድረግ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ (ICT Park) ቅጥር ግቢ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የመ/ቤቱ አመራርና መላው ሠራተኞችነገን ዛሬ እንትከል በሚል እንደሀገር እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በመሳተፍና የመርሐ ግብሩ አካል መሆናችንን በማረጋገጥ አሻራችንን አስቀምጠናል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከመንግስትና ከህዝብ በተልዕኮ ከተሰጠው ዋነኛ ኃላፊነት ባሻገር  ላለፉት አመታት እንደ ሀገር ሲተገበር በቆየው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በተለያየ ደረጃ ሲሳተፍ እንደቆየ አስታውሰው የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁ የመከታተል ስራዎችም ሲሰሩ መቆየታቸውን ዋና ኦዲተሯ ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም በዚህ ዓመት የተተከሉት ችግኞችም እንዲጸድቁ ከሚመለከታቸው የአስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት የክትትል ሥራ ይሠራል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተካላ መርሐ ግብር የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ከ1000 በላይ ችግኞች በፓርኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተተክለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *