News

የመ/ቤቱ ሰራተኞች ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን አከበሩ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሠራተኞች አጎራባች ከሆኑት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ሠራተኞች ጋር በመሆን በመ/ቤቶቹ ቅጥር ግቢ 18ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን አክብረዋል፡፡

በአከባበር ስነስርዓቱ ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በስነ-ስርኣቱ ላይ በመገኘት በዓሉን በማስመልከት አጭር ንግግር አድርገዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሶስቱም ተቋማት ትልቅ ሀገራዊ ተልእኮ ወስደው ኢትዮጵያ እንድትበለፅግና ከዓለም ሀገራት ቀድማ እንድትሰለፍ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ሁሉም በአንድነት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት፣ መበልፀግና ከፍታ ቀን ከሌሊት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው ይህን የባንዲራ ቀን ስናከብር እነዚህን ሀገራዊ ተልዕኮዎች ለመወጣት ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንድታንሰራራ፣ በዓለም ሀገራት ፊት ከፍ እንድትል፣ ለዜጎቿ ኑሮ ማቅለያ የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎች እንዲመቻችላቸው መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ጨምረው ጠቅሰው ለሀገሪቱ እድገት ጸንቶ መቆም ሁሉም ሰው በተሰማራበት ሙያ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይገባዋልም ብለዋል፡፡

በስነስርኣቱ ላይ በአካባቢው በሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የሰልፍ ስነ-ስርዓት በኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) የሰንደቅ አላማ መስቀል ስነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን የሶስቱም ተቋማት ሃላፊዎችና ሰራተኞች ታድመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *