የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት /ፌዋኦ/ አዲስ ለተቀጠሩ የክዋኔ ኦዲተሮች የትውውቅ /Induction /ሥልጠና ሰጠ፡፡
የፌዋኦ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ ታደሰ ሥልጠናው ከእቅድ እስከ ሪፖርት ሂደት ያሉ ማለትም የዕቅድ ዝግጅት፣ የኦዲት ክንውን፣ ሪፖርት ዝግጅት እና ክትትል ሥራዎች ላይ የተኮረ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በስልጠናው ላይ ስለክትትልና አከባቢ ኦዲት ምንነትና ዓለማ፣ የፌዋኦ የሰው ሀብት አስተዳደር እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማትና አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ መደረጉን አቶ አበራ አስረድተዋል፡፡
ሰልጣኝ ኦዲተሮችም በስልጠናው ለቀጣይ ሥራዎቻቸው ግብዓት የሚሆኑ ጠቃሚ ግብዓቶችን ያገኙበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሥልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት ከግንቦት 15 -19 ቀን 2014 ዓ.ም ለ28 ጀማሪ የክዋኔ ኦዲተሮች መሰጠቱ ታውቋል፡፡