News

አዲስ ለተሸሙት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳ አቀባበል ተደረገ

በቅርቡ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ሆነው ለተሸሙት ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳ በመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላትና መላው ሠራተኞች አቀባበል ተደረገ፡፡

ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በመ/ቤቱ በተካሄደው የአቀባበል ስነስርዓት ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤና  ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠን ጨምሮ የመ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳን አስተዋውቀው ስለመ/ቤቱ ተልዕኮና አጠቃላይ ሁኔታ  አጭር ገለጻ አድርገዋል፡፡

አዲስ ተሿሚው  ክቡር ም/ዋና ኦዲተር አቶ ሃጂ ኢብሳ በበኩላቸው ራሳቸውን በማስተዋወቅ  በመንግስት ተቋማት በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶችና ስራዎች ያገለገሉባቸውን የስራ ተሞክሮዎቻቸውን የገለጹ ሲሆን በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሹመት በመመደባቸው ደስታቸውን ገልጸው በመ/ቤቱ መልካምና ውጤታማ የስራ ጊዜ እንደሚኖራቸው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *