News

አነስተኛ ገቢ ላላቸው የመ/ቤቱ ሠራተኞች ለበዓል መዋያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሠራተኞች ክብብ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የመ/ቤቱ ሠራተኞች ለበዓል መዋያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

ሚያዚያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው ስነስርዓት ላይ በመገኘት ለሠራተኞቹ የገንዘብ ድጋፉን ያበረከቱት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር እና የክበቡ የበላይ ጠባቂ ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ናቸው፡፡

የመ/ቤቱ ዋና ኦዲተር  ጽ/ቤት ኃላፊና የሠራተኞች ክብብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወቀ ጤናው የገንዘብ ድጋፉን አስመልክተው ባደረጉት የመግቢያ ንግግር የገንዘብ ድጋፉ ሀሳብ ከክበቡ የበላይ ጠባቂ ክብርት ም/ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የመነጨ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ክብርት ም/ዋና ኦዲተር መሠረት በበኩላቸው የመ/ቤቱ የሠራተኞች ክብብ ቦርድ ሀሳቡን ተቀብሎ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመ/ቤቱ ሠራተኞች የገንዘብ ድጋፉን በማድረጉ አመስግነው ድጋፉ በቅርብ ቀናት በተከታታይ የሚከበሩትን የትንሳኤ እና የኢድ- አልፊጥር በዓላት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

መ/ቤቱ የመንግስት ተቋም እንደመሆኑ ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ ለሁሉም የመ/ቤቱ ሠራተኞች ማድረግ ባይቻልም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመ/ቤቱ ሠራተኞች በክበቡ በኩል የተደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውና መ/ቤቱ ለሠራተኞቹ ያለውን የአጋርነት መንፈስ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ የተደረገላቸው ሠራተኞች ለመ/ቤቱ የስራ አፈጻጸም ስኬት ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን የጠቆሙት ም/ዋና ኦዲተሯ ወደፊትም በስራ አካባቢ የሚታየው የአፈጻጸም ጥረት  ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ የተደረገላቸው ሠራተኞች በሰጡት አስተያየት የመ/ቤቱ የበላይ አመራር ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ተገንዝቦ ባቀረበው ሀሳብ  መሰረት  የሠራተኞች ክበቡ በአይዟችሁ ባይነት ላደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በበላይ አመራሩ በኩል እየተደረጉ ላሉት ሠራተኛውን ታሳቢ ያደረጉ ጥረቶች ከፍተኛ ከበሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *