News

አህጉራዊው የዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር በዋና ኦዲተር ሹመት የተሰማውን ደስታ ገለጸ

የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር (AFROSAI-E) ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሆነው በመሾማቸው የተሰማውን ደስታ ገለጸ፡፡
ማህበሩ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በላከው የደስታ መግለጫ ደብዳቤ የክብርት ዋና ኦዲተርን ሹመት ዜና በታላቅ ደስታ የተቀበለው መሆኑን ገልጾ “እንኳን ደስ አልዎ” በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር አባላት በሹመቱ ልባዊ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በላኩት የደስታ መግለጫ ደብዳቤ ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትም በመጪው ጊዜ በክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የስራ ልምድ እና የአመራር ብቃት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጠቀም የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር ዋና ጸሀፊ ሚስተር ኤም ኤም አር.ናካው በማህበሩ አባላት ስም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ አክለውም ክብርት ዋና ኦዲተር በተሾሙበት ታላቅ የኃላፊነት ቦታ ለሚገጥማቸው ሁሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የማህበሩ አባል የሆነው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሚያስፈልገው ድጋፍ ሁሉ አስፈላጊውን ጥረት እንደሚያደርጉ በማጠቃለያ መልዕክታቸው የጠቀሱት የማህበሩ ዋና ጸሀፊ በሹመቱ የተፈጠረው ዕድል ለተቋሙ አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ከክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ጋር ቀጥተኛ የስራ ግንኙነት እንዲኖር የሚያደርግና ቀጣይ የሆነና የቀረበ አብሮ የመስራት ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *