የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2015/2016 ኦዲት አመት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን የማስተዳደር ሥርዓት ለመፈተሽ ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት የታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙና ቅርሶችን በተሻለ ሁኔታ የማስተዳደር አሠራሮች እንዲጠናከሩ ተጠየቀ፡፡
ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ይፋዊ ውይይት መድረክ እንደተገለጸው ኦዲቱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን በውጤታማነት ለማስተዳደር የሚያስችሉ ተገቢ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና መለያ መስፈርቶችን በማዘጋጀትና በመተግበር ረገድ ጉልህ ክፍተቶች እንዳሉበት አሳይቷል፡፡
ከዚህም ሌላ በቅንጅታዊ አሠራሮች፣ በተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምዝገባና ልየታ፣ በቁጥጥርና ክትትል፣ በጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም ጥገና፣ በሙዚየሞች አደረጃጀት፣ በዘመናዊ መረጃ ስርዓት ትግበራ፣ ቅርሶችን በማስተዋወቅ፣ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ረገድ በባለስልጣን መ/ቤቱ አሠራር ላይ ጉድለቶች መታየታቸው በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የኦዲት ግኝቶቹን ለማሻሻል በባለስልጣን መ/ቤቱ የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲብራሩ ከመድረኩ ተጠይቆ የኢ. ፌ .ዴ ሪ. ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮች ከኦዲቱ በኋላ ግኝቶቹን ለማሻሻል በተወሰዱና በመወሰድ ላይ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የባለስልጣን መ/ቤቱን አመራሮች ምላሽ ተከትሎ ከም/ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኦዲት ግኝቶቹን ለማሻሻል በተወሰዱና መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች እንዲሁም ከባለስልጣን መ/ቤቱ አመራሮች በተሰጡ አጥጋቢ ያልሆኑ ምላሾች ዙሪያ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ኦዲቱ ትኩረት ያደረገባቸውን አበይት ጉዳዮች በማስቀደም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ከባለስልጣን መ/ቤቱ በኦዲት ግኝቶቹ እርምጃ አወሳሰድ ረገድ በመድረኩ የተሰጡ ከፊል ምላሾች በኦዲቱ ወቅትና በተለያዩ ጊዜያት ከተሰጡት ጋር የማይናበቡ በመሆናቸው ግልጽነት የጎደላቸው ናቸው ብለዋል፡፡
የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን ከእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አንጻር ለመለየት ባለስልጣን መ/ቤቱ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና የላብራቶሪ ግብአቶችን ለመጠቀም እያደረገ ያለው ጥረት በበጎ የሚታይ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ዝርዝር መመሪያ በማዘጋጀት፣ ሀገራዊ የቅርስ ጥበቃ ፖሊሲ አዘጋጅቶ በመተግበር፣ ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻል የቆየውን የመ/ቤቱን ማቋቋሚያ አዋጅ አሻሽሎ ማስፈጸሚያ ደንብ አዘጋጅቶ በመተግበር፣ በቅንጅታዊ አሠራር፣ በዳታ ቤዝ አደረጃጀትና ትግበራ፣ በቁጥጥርና ክትትል፣ በመረጃ አያያዝና ስርጭት እንዲሁም በሌሎች ክፍተቶች ዙሪያ ተጨማሪ የማሻሻያ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ ገልጸው መንግስት የተለያዩ የሀገሪቱን ቅርሶች ለጎብኚዎች ይፋ በማድረግ ረገድ የፈጠረውን እድል ተጠቅሞ ቅርሶችን በማስተዋወቅ በዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ሀገራዊ ጠቀሜታ ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ያለውን የስራ ትስስርና ስምምነት መሠረት በማድረግ የውጭ ጎብኚዎች ወደ ውጪ ይዘዋቸው የሚወጡ ቅርስ የሆኑና ያልሆኑ ነገሮች የሚለዩበትን አሠራር አጠናክሮ እንግልትን መቀነስና በቅንጅታዊ አሠራር ችግር ሳቢያ የሀገሪቱ ገጽታ እንዳይበላሽ በጉዳዩ ላይ ተገቢ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የተለያዩ ቅርሶችን የሚያካትተው የቱሪዝም ዘርፍ ከሀገሪቱ አምስት የኢኮኖሚ አውታሮች አንዱ በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ በመድረኩ ለተሰጡ የኦዲት ግኝት ማሻሻያ አስተያየቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት አሠራሩን የማሻሻል እርምጃውን እንዲያጠናክር ከቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
PAC-Stakeholders Public Hearing Demands Proper Working System to Manage Tangible Movable Heritages
The Public Expenditure Administration and Controlling Affairs Standing Committee of the Ethiopian Parliament and audit stakeholders’ public hearing requested the national movable heritages to be managed properly under focused attention by utilizing required legal frameworks & appropriate working mechanisms.
The public hearing, held on June 16 2015, stated in its discussion that the 2023/2024 audit year performance audit of the Office the Federal Auditor General (OFAG) uncovered a number of breaks in the working systems of the Ethiopian Heritage Authority in managing tangible movable heritages.
Based on the major tips of the audit report, mentioned in the hearing, the Authority lacks the necessary legal frameworks needed to administrate those movable heritages properly.
According to the discussion made in the public hearing, absence of joint works with target stakeholders; insufficient regulatory, follow up, maintenance and protecting systems; inadequate attention to promote and manage heritages through utilizing modern and digitalized information system, and lack of survey studies are also additional difficulties discovered by the audit.
In addition to useful and practical propositions by PAC members, stakeholders and OFAG officials H.E Mrs. Meseret Damtie, the Federal Auditor General, recommended profitable solutions that likely improve the findings through real commitment and attentive corrective actions.
Appreciating the attempts of the Authority in organizing and applying modern technologies and technical laboratories to identify the profile of different heritages, the Auditor General suggested further workable actions to be taken to provide and apply proper legal frameworks, cooperative works, more organized digitalized information systems, publicity drives and others in order to achieve operative and effective management systems for proper utilization of movable heritages across the nation.