የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለድጋፍ ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የፕሮጀክት አስተዳደር ሥልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው በፕሮጀክት ምንነትና ዓላማ፣ ዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራ፣ ክትትልና ግምገማ ላይ መሠረታዊ ግንዛቤ ያስጨበጠና በቀጣይ በተቋሙ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ውጤታማነት አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገጿል፡፡
በተለይም ስልጠናው የልማት ፕሮጀክቶች ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ ይዘቶች፣ ፕሮፖዛል አዘገጃጀት፣ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ፣ ጥራትና በጀት እንዴት እንደሚሠሩ፣ ፕሮጀክቶች የታለመላቸውን ዓላማ እንዲመቱ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት በምን መንገድ መተግበር እንዳለበት፣ ፕሮጀክቶች በትክክል ግባቸውን ስለመምታታቸው እንዴት እንደሚገመገሙ እና የአፈጻጸም ሪፖርት አደራረግ ሥርዓቱን በሚመለከት ሰፊ ግንዛቤ ያስጨበጠ ነው ተብሏል፡፡
በሥልጠናው የተሳተፉ የተቋሙ ሠራተኞችም በተሰጣቸው ሥልጠና መደሰታቸውን ገልጸው ተቋሙ ለሰው ሃብት ልማት እየሰጠ ያለውን ትኩረት ይበልጥ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በቢሾፍቱ ከተማ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ10 ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን በሥልጠናው የመ/ቤቱ የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳ/ት፣ የፋይናንስ፣ ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳ/ት፣ የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳ/ት እና የለውጥ ስራ አመራር ዳ/ት አመራርና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡