የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመ/ቤቱ ከፍተኛ የፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲተሮች በግንባታ ሂሳብ ኦዲት ላይ የተኮረ ሥልጠና ሰጠ፡፡
ከመጋቢት 08-12/2017 ዓ.ም ለ5 ቀናት በመ/ቤቱ የስልጠና ማዕከል በተሰጠው ስልጠና 111 ከፍተኛ ኦዲተሮች የተሳተፉ ሲሆን ዓለማውም በየጊዜው እያደገ የመጠውን የግንባታ ሥራ ታሳቢ ያደረገ እና ወቅቱ የሚጠይቀውን የግንባታ ሂሳብ ኦዲት እውቀትና ክህሎት ተላብሶ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ወቅት የግንባታ ሂሳብ ምንነትና የኦዲት ሂደቶች፣ የቅድመ ግንባታና የግንባታ ወቅት ግዢ ሂደት፣ የውል አስተዳደር፣ የግንባታ ሂሳብና ታክስ እና ሌሎች በግንባታ ወቅት ሊታዩ የሚገቡ ጉዳዮች መዳሰሳቸው የተገለጸ ሲሆን ኦዲተሮችም በሥራ ወቅት ያጋጠሟቸውን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ያላቸውን እውቀት ይበልጥ እንዲጎለብቱ ታስቦ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሚያከናውናቸውን የተለያዩ የኦዲት አይነቶች ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንዲያስችለው የኦዲተሮቹን ሙያዊ አቅም ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡