News

በኮምፕሊያንስ ኦዲት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመ/ቤቱ የፋይናሽያል ኦዲት ከፍተኛ ኦዲተሮች በኮምፕሊያንስ ኦዲት ላይ የተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሰ ሥልጠናው ቀጣይነት ያለው ሙያዊ የክህሎት ሥልጠና (Continuous Professional Development- CPD) አካል መሆኑን ጠቁመው በተለይም በዚህ ሥልጠና ተሳታፊ ኦዲተሮች ልምድ ያላቸው እንደመሆናቸው እርስ በርስ የመማማር እድላቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም ዓለም አቀፍ የኦዲት አሠራሮችን ተከትሎ መስራትና ስታንዳርዶችን በየጊዜው ከወቅቱ ጋር እያሻሻሉ መሄድ በኦዲት ሙያ የሚጠበቅ ነው ያሉት አቶ አበራ ስልጠናው ኦዲተሮቹ በኮምፕሊያንስ ኦዲት አተገባበር ላይ የነበራችውን እውቀት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ኢንስትራክተር አቶ ኢዮብ ጉታ በበኩላቸው ስልጠናው የ2017 የኦዲት ማንዋልን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ እና በዋናነት በኮምፕሊያንስ ኦዲት ምንነት፣ የአሠራር ስታንዳርድ እንዲሁም ከሌሎች የኦዲት ዓይነቶች ባለው ልዩነት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ከመስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም  የተሰጠ ሲሆን ከ 80 በላይ የተቋሙ ከፍተኛ ኦዲተሮች በስልጠናው ተሳታፊ መሆናቸውን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *