የኦዲት ረቂቅ ሪፖርትን ጥልቀት ባለው ሁኔታ መከለስና መገምገም የሚያስችል (Critical Reviewing a Draft Audit Report) እንዲሁም በኦዲት ቡድኖች አመራር (Leading & Managing Teams) ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡
ከሚያዚያ 3-4 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደው ስልጠና በአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስር ከሚገኘው የአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE- Center of Audit Excellency) በመጡ የስልጠና ኤክስፐርቶች የተሰጠ ነው፡፡
ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጠው የመጀመሪያ ቀን ስልጠና በኦዲት ረቂቅ ሪፖርት ጥልቅ ክለሳና ግምገማ ላይ ያተኮረ ሲሆን በስልጠናው 35 የሚሆኑ ከኦዲት ዳይሬክተር እስከ ከፍተኛ ኦዲተር የሚገኙ ሰልጣኞች ተሳትፈውበታል፡፡
ሚያዚያ 4 ቀን 2015 የተሰጠውና በኦዲት ቡድኖች አመራር ላይ ያተኮረው የሁለተኛ ቀን ስልጠናም ቀደም ሲል በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የተሰጠውን ስልጠና ያልወሰዱ ከ25 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ ኦዲተሮች የተሳተፉበት ነው፡፡
በአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስር የሚገኘው የአሜሪካ የኦዲት ልህቀት ማዕከል ባለፉት ጊዚያት በ “ኦን ላይን” ከሰጣቸው ስልጠናዎች ባሻገር የስልጠና ኤክስፐርቶቹን በአካል በመላክ ቀደም ባሉት ጊዜያትም የመ/ቤቱን የኦዲት አሠራር በተለያየ መልኩ ሊያጠናክሩ የሚችሉ ቴክኒካል ሥልጠናዎችን መስጠቱ ታውቋል፡፡