News

በኤች. አይ. ቪ. ስርጭትና መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሠራተኞች በኤች. አይ. ቪ. ስርጭትና መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄዱ፡፡

ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ቋሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ላይ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኤች. አይ. ቪ. ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለና በጉዳዩ ላይ ያለው የህብረተሰቡ ትኩረትም የሚፈለገውን ያህል ያለመሆኑ በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡

መድረኩን የመሩት የመ/ቤቱ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ታመነ ጌታሁን በውይይቱ የተነሱትን መሰረታዊ ነጥቦች አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በመ/ቤቱ ሠራተኞች ዘንድ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የመከላከሉን ስራ ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *