News

በአካታችነት ኦዲት ትግበራ መስፈርት ዝግጅት ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተካሄደ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከኦድዋስ (Organization for Development of Women and Children in Ethiopia: ODWaCE) ጋር በመተባበር የአካታችነት ኦዲት ትግበራ መስፈርት /ቼክሊስት/ ዝግጅት ላይ ያተኮረና ከመጋቢት 22/2017ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የቆየ ወርክሾፕ አካሂዷል፡፡

በወርክሾፑ በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከቱ ህጎች እና የአሠራር ሥርዓቶች ዙሪያ ለተሳታፊዎች የግንዛቤ ማጨበጫ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡

ገለጻውን ተከትሎ የፋይናሺያልና የክዋኔ አካታችነት ኦዲት ትግበራን ለመመርመር የሚያስችል መስፈርት/ቼክሊስት/ በሁለቱም የኦዲት ዘርፎች የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይ የተዘጋጀውን መስፈርት ይበልጥ በማዳበር ሥራ ላይ እንደሚውል ከመ/ቤቱ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለሁለት ቀና በተካሄደው ወርክሾፕ 15 የሚሆኑ የመ/ቤቱ የኦዲት ዳይሬክተሮችና ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል፡፡

በአካታችነት ኦዲት ትግበራ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከዚህ ቀደምም በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የመ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *