የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከአይፓስ ኢትዮጵያ (IPAS Ethiopia) ጋር በመተባበር የአካታችነት ኦዲት ትግበራ ላይ ያተኮረ የ 2 ቀናት ሥልጠና አካሂዷል፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ ጤናው ሥልጠናው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚሰራቸው የኦዲት ሥራዎች የአካታችነት ኦዲትን ዓለም አቀፍ የኦዲት ስታንዳርዶችን ጠብቆ ለመተግበር ዓለማ የደረገ መሆኑን በስልጠናው መክፈቻ ላይ ጠቅሰው ሰልጣኝ ኦዲተሮች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ እና ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደተግባር እንዲለውጡ አሳስበዋል፡፡
ሥልጠናው በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የተመለከቱ ህጎች እና የአሠራር ሥርዓቶች በተመለከተ እንዲሁም የአካታችነት ኦዲት መተግበር በሚያስችሉ የኦዲት መመዘኛ መስፈርቶች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ከመ/ቤቱ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው ሥልጠና 105 የፋይናንሻልና ህጋዊነት ኦዲት እንዲሁም የክዋኔ ኦዲት ከፍተኛ ኦዲተሮች እንደተሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአካታችነት ኦዲት ትግበራ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከዚህ ቀደምም በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የመ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡