News

በተለያዩ የኦዲት አሠራሮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና ለሌሎች የግል የኦዲት ተቋማት የኦዲት ስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተለያዩ የኦዲት አሠራሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም አስከ ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ  በተሰጠው ስልጠና ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ ከኦዲት አገልግሎት ኮርፖሬሽንና ከሌሎች የግል የኦዲት ተቋማት የተውጣጡ ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE- Center of Audit Excellency) የተዘጋጀና የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የተለያዩ ሰልጣኞች በተሳተፉባቸው በእያንዳንዳቸው የስልጠና ቀናት የተለያዩ የኦዲትና ኦዲት ነክ አሠራሮችን የተመለከቱ የስልጠና ርዕሶች የተሸፈኑ ሲሆን ቡድኖችን መምራትና ማስተዳደር (Leading & Managing Teams) በሚል ርዕስ በቀረበው ስልጠና 15፣ በፋይናንሽያል ኦዲት የስጋት ግምገማና ምላሽ አሰጣጥ( Assessing & Responding to risks in a Financial Statement audit)-17 ፣  በኦዲት ሪፖርት ረቂቅ ጥልቅ ክለሳ (Critically reviewing Draft Report)-18፣ በግዥ አፈጻጸም ማጭበርበር ( Procurement Fraud)-15 እና በውጤታማ የኦዲት ግኝት አስተያየት አጻጻፍ ( Writing effective Audit recommendation)- 20 በጥቅሉ 85 ሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ስለ ስልጠናው ሂደት አስተያየታቸውን የሰጡት ተሳታፊዎች ስልጠናው በኦዲት ስራ አፈጻጸማቸው ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንና በሙያቸው ዙሪያ ቀደም ሲል ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ልህቀት ማዕከል (CAE- Center of Audit Excellency) ቀደም ባሉት ጊዜያትም ለመ/ቤቱ የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *