News

በስርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት እና ማህበራዊ አካታችነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በስርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካታችነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ፡፡

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ቀን የተካሄደውን ስልጠና አዘጋጅቶ የሰጠው የመ/ቤቱ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሲሆን 50 የሚሆኑ የመ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በስልጠናው መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

ስልጠናው በዋናነት የስርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት እና ማህበራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መ/ቤቱም ሆነ በስሩ የሚገኙ የስራ ክፍሎች ከዕቅድ ጀምሮ ሊያከናውኗቸው በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ግንዛቤን ያስጨበጠ ሲሆን ማህበራዊ አካታችነት፣ የስርኣተ ጾታ ማካተት እና የአካል ጉዳተኝነት ጽንሰ-ሀሳብና አካታችነት በሚሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ስር ዝርዝር የሆኑ ማብራሪያዎችና ገለጻዎች ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ በርካታ ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ለመ/ቤቱ ሠራተኞች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በተጓዳኝ ለሠራተኞች የሚቀርቡ የፍጆታ ዕቃዎችንና ቁሳቁሶችን በሚመለከታቸው አቅራቢ ድርጅቶች እንዲቀርቡ በማድረግ፣ ለሴት ሰራተኞች የትምህርት እድሎችን በማፈላለግ እንዲሁም የመ/ቤቱን ውጤታማ የህጻናት ማቆያ በማደራጀትና በመምራት እና ሌሎች ተዘማጅ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማስተባበር ጉልህ የስራ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *