በፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀና የስርአተ ፆታ እና የስርዓተ ፆታ ማከተትን ጽንሰ ሀሳብ መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ተሰጠ፡፡
ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለግማሽ ቀን በተሰጠው ስልጠና ላይ የመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን የመ/ቤቱ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽጌ ጥላሁን ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው የስርዓተ ጾታ ምንነት፣ የስርዓተ ጾታ ማካተት ጽንሰ ሀሳብ፣ ትርጉምና አተገባበርን የተመለከቱ ዝርዝር ሀሳቦች የቀረቡበት መሆኑ ታውቋል፡፡