News

መ/ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቀረበ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት አፈጻጸሙን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቀረበ፡፡

በክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የቀረበው ሪፖርት የመ/ቤቱን የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት አፈጻጸምና በ2015 በጀት ዓመት በተቋሙ የተከናወኑ ሌሎች ክንውኖችን ያካተተ ነው፡፡

በክብርት ዋና ኦዲተሯ በቀረበው ዝርዝር የኦዲት ሪፖርት መሠረት መ/ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በተለያዩ ተቋማት ላይ በካሄደው የፋይናንሽያልና የክዋኔ ኦዲት መሰረት በርካታ የኦዲት ግኝቶች መታየታቸው ተገልጿል፡፡

በኦዲት ግኝቶቹ መሠረት ለኦዲት ተደራጊ ተቋማቱ ከመ/ቤቱ በተሰጡ የማሻሻያ እርምጃ አስተያየቶች መሰረት በርካታ የማሻሻያ እርምጃዎች መወሰዳቸው የተጠቀሰ ሲሆን በተለይም ተሰብሳቢ ሂሳቦችን በተመለከተ የተሰበሰቡና ያልተሰበሰቡ ገንዘቦች በሪፖርቱ በአኃዝ ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም ህግን ያልተከተሉ ወጪዎች፣ ህግና መመሪያን ያልተከተሉ ክፍያዎች፣ አሠራርን ያልተከተሉ የሂሳብ አመዘጋገቦች፣ በጊዜያቸው መከፈል የነበረባቸውና ያልተከፈሉ ሂሳቦች፣ የአጠቃቀም ችግር ያለባቸው በጀቶች እና ህገ ወጥ ግዥዎች እንዲሁም በርካታ የንብረት አስተዳደር ጉድለቶች በተለያዩ ተቋማት ላይ በኦዲቱ መታየታቸውና ለእነዚህም ግኝቶች የኦዲት ማስተካከያ አስተያቶች መሰጠታቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህም ሌላ መ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ያካሄዳቸው የክዋኔ ኦዲቶች በሪፖርቱ በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ለኦዲት ግኝቶቹም ተገቢ የኦዲት ማስተካከያ አስተያየቶች መሰጠታቸው ተገልጿል፡፡

ከሪፖርቱ በኋላ ከም/ቤት አባላት የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው በክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን በሪፖርቱ መሠረት የተለያዩ ጉድለቶች በታዩባቸው ተቋማት እና አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን ም/ቤቱም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ክብርት ዋና ኦዲተሯ ጠይቀዋል ፡፡

የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ሙሉ የሪፖርቱን ሂደት ይከታተሉ!

https://www.facebook.com/hoprparliament/videos/813819123465074

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *