የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ15 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እንዲሁም ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ 34 ወንበሮችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ሚያዚያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በመ/ቤቱ በተከናወነው የርክክብ ስነስርዓት ላይ ኮምፒውተሮቹን ያስረከቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኢንፎርሜሽን ሲስተም ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይግረም መንገሻ ሲሆኑ የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሚር የሱፍ የኮምፒውተር ድጋፉን ተረክበዋል፡፡
በሌላ በኩል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተደረገውን የቢሮ መገልገያ የወንበር ድጋፍ የተረከቡት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ወ/ገብርኤል ናቸው፡፡
መ/ቤቱ ቀደም ባሉት ጊዜያት በርካታ የላፕቶፕና የተለያዩ የስራና የቢሮ መገልገያዎችን በተመሳሳይ መልኩ ለሌሎች የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችና ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት በድጋፍ መልክ አበርክቷል፡፡

