የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ተቋማዊ የሥርዓተ ጾታ አካቶ ትግበራ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር አድርጓል፡፡
የመግባቢያ ስምምነት መርሃግብሩ የተከናወነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በስርዓተ ጾታ አካቶ ትግበራ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ተቋማት ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እውቅና በሰጠበት መድረክ ሲሆን የመግባቢያ ስምምነት ፊርማውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጌጎ ተስፋዬ (ዶ/ር) አካሂደዋል፡፡
ስምምነቱ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 982/2008 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በሚያከናውናቸው የክዋኔ ኦዲቶች ውስጥ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን በሚመለከት በኦዲት ተደራጊ ተቋማት በኩል ሊከናወኑ የሚገባቸውን የአካቶ ተግባራት አፈጻጸም አስመልክቶ የሚያካሂደውን ኦዲት ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል ስራ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት መሆኑን የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ያሳያል፡፡
Memorandum of Understanding to Perform Audit of Gender Mainstreaming Well
The Ethiopian Office of the Federal Auditor General, OFAG made a mutual working deal with the Ministry of E.F.D.R.E Women and Social Affairs to work together on the process, impacts and outcomes of the auditing tasks performed in the areas of gender and other social groups’ mainstreaming.
An agreement that bases Memorandum of Understanding (MOU) has been signed by the Federal Auditor General H.E Meseret Damtie & H.E Ergoge Tesfaye( PhD), the Minster, E.F.D.R.E Women and Social Affairs on August 29,2024, and both officials publicized their institutions technically help each other make the auditing engagements carried out on gender and other social groups mainstreaming more efficient & effective.