የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለጉምሩክ ኮሚሽን የውስጥ ኦዲተሮች በፋይናንሻል ኦዲት ላይ ያተኮረ 2ኛ ዙር ስልጠና ሰጠ፡፡
ለ5 ቀናት የተሰጠው ስልጠና በዋናነት በውስጥ ቁጥጥር ግምገማ፣ በስጋት ዳሰሳ ጥናት፣ በናሙና አወሳሰድ፣ በኦዲት ወረቀቶች አግባብነት እንዲሁም በኦዲት ሪፖርት አዘገጃጀት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተኮረ እንደነበር ስልጠናውን የሰጡት አቶ አህመድኑር ስዋልሂ እና አቶ ቴዎደሮስ ሽመልስ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሚሽኑ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዩሐንስ መለሰ ስልጠናው ውጤታማ እንደነበር ገልጸው በአዲሱ የውስጥ ኦዲት ማኑዋል መሰረት የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቶቻቸውን ይበልጥ ለማጠናከር አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኝ ኦዲተሮች በበኩላቸው ስልጠናው ለስራቸው በጣም ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች እያዘጋጀ ባለሙያዎችን ለማብቃት እያደረገ ያለው ሥራ ተጠናሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
ከጥር 02 እስከ ጥር 06 ቀን 2015 ዓ.ም በተሰጠው ሥልጠና ለ37 ከተለያዩ የተቋሙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተውጣጡ ኦዲተሮች የተሳተፉ ሲሆን በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ዙር በአጠቃላይ 70 ኦዲተሮች ማሰልጠን መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡