የፌዴራል ዋና ኦዲተር /ፌዋኦ/ መ/ቤት ለጉምሩክ ኮሚሽን የውስጥ ኦዲተሮች የፋይናንሻል ኦዲት ላይ ያተኮረ ስልጠና ከህዳር 05-09 ቀን 2015 ዓ.ም ሰጠ፡፡
የሥልጠናው ዓላማ የመ/ቤቱ የውስጥ ኦዲተሮች የዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲት ስታንዳርድ ተከትለው እንዲሠሩ ለማስቻል እና አዲሱን የውስጥ ኦዲት ማንዋል ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ እንደሆነ ከፌዋኦ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም የውስጥ ቁጥጥርን ለማሳደግ፣ ስጋትን መሰረት ያድረገ ኦዲት ለመስራት እንዲሁም የኦዲት ናሙናን ተግባራዊ በማድረግ ሌሎች የኦዲት ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናው በተግባር የተደገፈ እና አሳታፊ እንደነበር የገለጹት ሰልጣኝ ኦዲተሮች የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ላደረገው የስልጠና ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች ዕድሉን ላላገኙ ኦዲተሮች ስልጠናው እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል፡፡
ለ5 ቀናት በተሰጠው ስልጠና በአጠቃላይ 40 ከተለያዩ ቅርንጫፍ እና ከዋናው የጉምሩክ ኮሚሽን መ/ቤት የተውጣጡ ከጀማሪ እስከ ቡድን መሪ ያሉ ኦዲተሮች እንደተሳተፉበት ከፌዋኦ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡