News

መ/ቤቱ ለአባይ ባንክ የውስጥ ኦዲተሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአባይ ባንክ የውስጥ ኦዲተሮች የክዋኔ ኦዲት አሠራር ላይ የተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከመስከረም 20 – 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው ሥልጠና 18 የሚሆኑ የባንኩ የውስጥ ኦዲተሮች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በክዋኔ /Performance/ ኦዲት ምንነት እና ከእቅድ እስከ ሪፖርት ዝግጅት ያለውን የአሠራር ሂደት ላይ ያተኮረ መሆኑን ከመ/ቤት የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዋናው የኦዲት ሥራ ተግባሩ ባሻገር ከተለያዩ ተቋማት በሚቀርብለት የሥልጠና ፍላጎት ጥያቄ መሠረት በኦዲትና ኦዲት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *