News

መስሪያ ቤቱ የኦዲት ክትትልና ድጋፍ አሠጣጥ በሚመለከት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአማራ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ባለሙያዎች የኦዲት ክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከመስከረም 08-15 ቀን 2017 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ በተሰጠው ሥልጠና 25 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናሽያል፣ የክዋኔ እንዲሁም የኦዲት ምርምርና ስርጸት ስራ አስኪያጆችና ዳይሬክተሮች የተሳተፉበት ሲሆን ስልጠናው የመስክ ኦዲት ክትትል፣ ዶክመንት ክለሳ፣ የኦዲት ግብረመልስ አሰጣጥ፣ ኦዲተሮችን ማብቃት፣ የኦዲት ቡድን ግንባታና የአመራርነት ክህሎት እና የመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ሥራውን በተለያዩ አግባቦች አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

       

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *