ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅምንት አባላት ከታህሳስ 14-19/2015 ዓ.ም ሲሠጥ የቆየው የአመራነት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ስልጠናው በአስተሳሰብ ግንባታ /Mindset/, በአመራር ክህሎት /Leadership/፣ በስሜት ብልህነት /Emotional Intelligence/ እና በሌሎች ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
በስልጠናው መዝጊያ መልዕክት ያስተላለፉት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ስልጠናውን ለማኔጅመንት አባላት በበጎ ፈቃድ ለሰጡት የሰይድ እና እሱባለሁ የምክርና የሥልጠና አገልግሎት ህብረት ሽርክና ማህበር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በማህበሩ ለመ/ቤቱ የማኔጅመንት አካላት የተሰጠው ስልጠናም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ራሱን ለመለወጥና አሠራሩን ለማዘመን ለጀመረው ጥረት ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ዋና ኦዲተሯ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በስልጠናው የተገኘውን እውቀትና መነሳሳት ወደተግባር በመለወጥ ራስንና ሀገርን የሚለውጥ ነገር ለመስራት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግም ክብርት ወ/ሮ መሠረት ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ የመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት የ5 ቀኑ ሥልጠና ለግል ህይወታቸውም ሆነ ለሥራቸው የሚጠቅሙ ጠቃሚ የህይወት ክህሎቶችን የቀሰሙበትን እንደሆነ ገልጸው በቀጣይ በስልጠናው ያገኙትን አቅም ወደሥራ ለመለወጥ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡