የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በገቢ፣ በኮንስትራክሽን፣ በልዩ ኦዲትና በኦዲት ሙያ ስነ-ምግባር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከሰኔ 27 -29 ቀን 2017 ዓ.ም ለ 3 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አርባ ምንጭ ከተማ የተሰጠው ስልጠና ከላይ የተሰጡትን የስልጠና ይዘቶች መሠረት አድርጎ በፋይናንሻልና ህጋዊነት እና በክዋኔ ኦዲት 46 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮችና የኦዲት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን የተሳተፉበት መሆኑን ከመ/ቤቱ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡