በፌዴራል ዋና ኢዲተር መ/ቤት ለአንድ ሳምንት ለክዋኔ ኦዲተሮች ሲሰጥ የነበረው የአከባቢ ኦዲት ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በሥልጠናው ማጠናቀቂያ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ዘርፍ ም/ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናውን ለመስጠት ከአፍሪካ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ዋና ኦዲተሮች ማህበር /AFROSAI_E/ የመጡትን አሠልጣኞች፣ ማህበሩን እና ስልጠናውን በንቃት የተከታተሉትን ሁሉንም ኦዲተሮች አመስግነዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ መሠረት አያይዘውም ሠልጣኝ ኦዲተሮች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት በኦዲት ሥራቸው በአግባቡ ተፈጻሚ በማድረግ የኦዲት ጥራትን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
የመ/ቤቱ የአከባቢ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሻሾ መኮንን በበኩላቸው ሥልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው ጠቁመው ኦዲተሮችም የአከባቢ ኦዲት ማንዋሎችን በቀጣይነት ሊያነቡ እና በሥራቸው ወቅትም ትኩረት ሰጥተው በመሥራት ተገቢውን እውቀትና ክህሎት ሊያዳብሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ሠልጣኝ ኦዲተሮችም በሥልጠና ቆይታቸው የኦዲት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ በርካታ ጠቃሚ እውቀቶችን ማግኘታቸውን ገልጸው በተለይም ሥልጠናው ከዚህ ቀደም የአከባቢ ኦዲት ሲሠሩ የሚያገኙትን መረጃ ለመለካት ይቸገሩባቸው የነበሩ ችግሮችን ሊቀርፍላቸው የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናው ከአፍሪካ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ዋና ኦዲተሮች ማህበር በመጡ ሁለት አሠልጣኞች ለተከታታይ 5 ቀናት የተሰጠ ሲሆን ከ70 በላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክዋኔ ኦዲተሮች ተሳትፈውበታል፡፡