News

ለክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል

ፌ.ዋ.ኦ፡ ሰኔ 26 ቀን 2017፡- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፋይናንሻልና ህጋዊነት እንዲሁም ክዋኔ ኦዲተሮች የኦዲት ሱፐርቪዥን እና ግምገማን በሚመለከት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከሰኔ 23 – 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለ 3 ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ በተሰጠው ስልጠና በፋይናንሽያልና ህጋዊነት 37 እንዲሁም በክዋኔ ኦዲት 10 በአጠቃላይ 47 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮችና የኦዲት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠናው በኦዲት ሱፐርቪዥን እና ግምገማ ላይ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ታስቦ የተሰጠ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልልና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ጠንካራ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *