በሀገር ውስጥ ገቢ ታክስ ኦዲት አሰራር ላይ ያተኮረ ስልጠና ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የገቢዎችና ጉምሩክ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ኦዲተሮች ተሰጠ፡፡
ከመጋቢት 1 እስከ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም በመ/ቤቱ የሥልጠና ማዕከል የተሰጠው ስልጠና የንግድ ትርፍ ገቢ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ኤክሳይስ ታክስ እና ትርፍ ክፍፍል ገቢ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ የጉምሩክ ቀረጥ ታክስ እና በአገር ውስጥ ግብር ላይ ያለው የኦዲት አሰራር ተመሳሳይና ወጥነት እንዲኖረው ለማስቻል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተጨማም ኦዲተሮቹ በጉምሩክና የሀገር ውስጥ ገቢ ታክስ ኦዲት ላይ መረጃን የመተንተንና ወደ ውጤት የመቀየር ክህሎታቸውን ማዳበር እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል::
በስልጠናው 43 የገቢዎችና ጉምሩክ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን መ/ቤቱ የውስጥ የስልጠና አቅምን ተጠቅሞ የሰራተኛውን ክህሎት ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡