ኦዲት ለዜጎች ተጠቃሚነት

ስለ ፌዋኦ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሀገሪቱ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ዜጎችን ለማገልገል በስራ ላይ የሚያውሏቸው የመንግስትና የህዝብ የፋይናንስና ቁሳዊ ሀብቶች በህግ፣ በደንብና መመመሪያ መሰረት በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውን በህጋዊ ኦዲት በማረጋገጥ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር እንዲጎለብት እንዲሁም በመንግስት ተቋማት አሠራር ላይ የመልካም አስተዳደር ስርዓት በአግባቡ እንዲረጋገጥ ለማድረግ የተቋቋመ እና ከ80 አመታት በላይ የኦዲት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ነፃና ገለልተኛ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡

የመ/ቤቱ ተጠሪነት በዋናነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲሆን ተቋሙ የፌዴራል መንግስቱን የኦዲት ስራዎች እንዲያከናውን በሀገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 101 እና አሁን በስራ ላይ ባለው የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 982/2008 እንዲሁም የተወሰኑ የአዋጁን አንቀጾች ለማሻሻል በወጣው የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1146/2011 በተሰጡት ስልጣንና ኃላፊነቶች መሠረት የኦዲት ስራውን በውጤታማነት በማከናወን ውጤቱንም በተደራጀ የኦዲት ሪፖርት ተጠሪ ለሆነለት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ማድረግን ጨምሮ ሌሎች በህግ የተሰጡትን ተግባራት የሚያከናውን ነው፡፡

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ምሳሌ የሆነ የኦዲት ተቋም በመሆን ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማጠናከር አስተዋፅዖ በማበርከት የኢትዮጵያ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ።

ተልዕኮ

በዓለም አቀፍ የከፍተኛ የኦዲት ተቋማት መመዘኛዎች መሠረት ገለልተኛ የኦዲት አገልግሎቶችን በማከናወን የመንግሥት ተቋማት የተልዕኮ አፈጻጸምን እና መልካም አስተዳደርን ለማጠናከር አስተዋፅዖ ማበርከት።

እሴቶች

የእኛ ስኬቶች

የፌዴራል ዋናኦዲተር ቤት (ፌዋኦ) በዋናነት የአገሪቱን የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ድርጅቶችን ሂሣብ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል።

0%

የኦዲት ጥራት

100%

የሂሳብ እና ህጋዊነት ኦዲት

60%

የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት

100%

ልዩ ኦዲት

60%

የክዋኔ ኦዲት

10%

የመረጃ ስርዓት ኦዲት

72%

አጠቃላይ የኦዲት ሽፋን

የህግ ማዕቀፎች

ስልጣናችንን እና የሪፖርት ማቅረቢያ መዋቅራችንን የሚወስኑ ዋና ዋና የህግ ማዕቀፎችን እና መሰረታዊ ሰነዶቻችን ይመልከቱ። ለመልካም አስተዳደር እና ተጠያቂነትን መነሻ የሆኑ አዋጆችን፣ ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎችን እና የሪፖርት ማቅረቢያ መመሪያዎችን ይመልከቱ።

እኛን ለማወቅ ፍላጎት አለዎት?

የማኔጅመንት አባላትን ይተዋወቁ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ማኔጅመንት በሀገራችን ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን እንዲሁም የህዝብ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው።

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጥልቅ ቁርጠኝነትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ያቀፈው ማኔጅመንታችን፣ የተቋሙን እምነት እና ታማኝነት የሚያጎለብቱ አስተማማኝ የኦዲት ሪፖርቶችን ለማቅረብ ሁልጊዜም ተግቶ ይሰራል፡፡

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ጥያቄ አለዎት? መልስዎን በተደጋጋሚ ከሚጠየቁ ጥያቄዎቻችን ዝርዝር ውስጥ ያግኙ! ጥያቄዎ በእኛ ዝርዝር ውስጥ ከሌለ፣ እኛን ለማግኘት እና የሚፈልጉትን መረጃ ለማግኘት ጥያቄዎትን በነጻነት ይላኩልን!

ክፍት የስራ ቦታዎች እና ማስታወቂያዎች

የመ/ቤታችን አካል ይሁኑ!