










ክብርት መሰረት ዳምጤ
የዋና ኦዲተር መልክት
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 101 እና በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 982/2008 እንዲሁም በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1146/2011 መሰረት የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ለመወጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
የመ/ቤቱ ተጠሪነት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲሆን የህዝብና የመንግሥት ሀብትና ንብረት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እና ይህንን ተግባር የመፈጸምና የማስፈጸም ተልዕኮ የተሰጣቸው የመንግሥት ተቋማትም ለተግባራዊነቱ በመትጋት ግልፅነትና ተጠያቂነትን እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ሊያሰፍን የሚችል አሠራር እንዲከተሉ ለማድረግ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ ይገኛል።
አድዋ መሰረት ዳምተ
የዋና ኦዲተር መልክ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 101 እና በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 982/2008 እንዲሁም በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1146/2011 መሠረት የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ለመወጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
የመ/ቤቱ ተጠሪነት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲሆን የህዝብና የመንግሥት ሀብትና ንብረት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እና ይህንን ተግባር የመፈጸምና የማስፈጸም ተልዕኮ የተሰጣቸው የመንግሥት ተቋማትም ለተግባራዊነቱ በመትጋት ግልፅነትና ተጠያቂነትን እንዲከተሉ ለማድረግ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ ይገኛል።
በፌዴራል መንግስት ተቋማት እና ድርጅቶች ላይ የፋይናንሽያል፣ የክዋኔ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የቁጥጥር፣ ልዩ ኦዲቶችንና ሌሎች ኦዲቶችን በማድረግ የተቋማቱ አሠራራሮች በህግ አግባብ እንዲከናወኑና እንዲመሩ እንዲሁም በየዘርፉ የሚታዩ የኦዲት ግኝቶች በወቅቱ እንዲታረሙ የማድረግ ተልዕኮውን እያተገበረ ይገኛል።
ለተልዕኮው ስኬታማነትም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት በርካታ የኦዲት ግኝቶች በየደረጃቸው እንዲታረሙና አጥፊዎችም በሚመለከታቸው የፍትህ አካላት አማካይነት በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተጨባጭ እና ተአማኒ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በማመንጨት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አስተዋጽኦዎችን እያበረከተ ነው።
መ/ቤቱ ስራውን በብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ ዘመኑ የሚጠይቀውን የዘመናዊ መሣሪያ ግብአት በየወቅቱ በመሟሟትና የመ/ቤቱን አመራርና ሠራተኞች ሙያዊ ዕውቀት ለማዳበር የሚያስችሉ ተቋማዊ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ስልጠናዎችን በማመቻቸት ስራውን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የተቋሙ የኦዲት ስራ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የተለያዩ የዓለም አቀፍ የኦዲት ስራ ሰታንዳርዶችን ያሳለጠ እንዲሆን ከተለያዩ የአለም አቀፍ የኦዲት ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር አሠራር እያጠናከረ ይገኛል። ለዚህም ከእንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገሮች ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ማህበር (AFROSAI-E) ጋር እያከናወነ ያለው ተግባር በዋቤነት የሚጠቀስ ነው።
በሰው ሀይል ረገድ ብቁ ሙያተኞችን ለሟሟላት ጥረት እያደረገ ቢሆንም ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያየዘ የብቁ ሙያተኞች ፍልሰት በመኖሩ ይህንን ችግር መቅረፍ በሚያስችል ሁኔታ ላይ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጥያቄዎቹን በማቅረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
በየአምስት ዓመቱ የሚከልሳቸውን ወቅታዊውን የተቋሙን እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረጉ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን መሰረት ያደረጉ ዓመታዊ ዕቅዶቹን መላውን ሠራተኛ ባሳተፈ መልኩ በማዘጋጀት እና አፈጻጸማቸውንም በመገምገም ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መሠረት ባለፉት ዓመታት ባደረጋቸው ጠንካራ ጥረቶች የፋይናንስና ህጋዊነት ኦዲቱን ሽፋን ወደ 100% እንዲሁም የክዋኔ ኦዲት ሽፋኑን ወደ 26% ማሳደግ ችሏል።
በአሁን ሰዓትም ከ2013 እስከ 2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን ተቋማዊ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በመንደፍና ይህኑን ወደ ዓመታዊ ዕቅዶች በማውረድ አመርቂ አፈጻጸም እያስመዘገበ ነው። ለዚህም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አማካይነት የኦዲት ተደራጊ ተቋማት የኦዲት ግኝቶችን በተመለከተ በየጊዜው የሚካሄዱ ይፋዊ የህዝብ መድረክ ውይይቶችና ከውይይቶቹም እየተገኙ ያሉ ግብረ መልሶች ለውጤታማ አፈጻፀሙ ማሳያ ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በኦዲት ስራው ላይ ውጤታማ ስኬቶች እያስመዘገበ ያለው መ/ቤቱ በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ የሚገጥሙትን የተለያዩ ተግዳሮቶች በመቅረፍ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር ወደፊትም በዕቅድ አፈጻጸማችን ላይ ሊገጥሙ በሚችሉ የአሠራር ተግዳሮቶች ላይ ቀድሞ በመዘጋጀትና የመፍትሔው አካል በመሆን የበለጠ ስኬት እንደምናስመዘግብ እመነቴ የፀና ነው። መ/ቤቱ ከተጣለበት የህዝብንና የሀገርን ሀብት ከብልሹ አሠራርና ከብክነት የመጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ አደራና ተልዕኮ እንዲሁም ለሌሎች የጥሩ አፈጻጸም ምሳሌ ከመሆን አንጻር የእያንዳንዱ የተቋሙ አመራርና ሠራተኛ እንቅስቃሴም ከብልሹ አሠራር እና ከዳተኝነት የጸዳ እና የበለጠ ፍጹም በሆነ ሙያዊና ሞራላዊ ስነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን አደራዬን አስተላልፋለሁ።
አመሰግናለሁ።
መሠረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር
የቅርቡ ዜናዎች
የቅርብ ጊዜ ዓመታዊ ሪፖርቶች
ስለ እኛ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሀገሪቱ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ዜጎችን ለማገልገል በስራ ላይ የሚያውሏቸው የመንግስትና የህዝብ የፋይናንስና ቁሳዊ ሀብቶች በህግ፣ በደንብና መመመሪያ መሠረት በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውን በህጋዊ ኦዲት በማረጋገጥ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር እንዲጎለብት እንዲሁም በመንግስት ተቋማት አሠራር ላይ የመልካም አስተዳደር ስርዓት በአግባቡ እንዲረጋገጥ ለማድረግ የተቋቋመ እና ከ80 አመታት በላይ የኦዲት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ነፃና ገለልተኛ መንግስታዊ ተቋም ነው።
የመ/ቤቱ ተጠሪነት በዋናነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲሆን ተቋሙ የፌዴራል መንግስቱን የኦዲት ስራዎች እንዲያከናውን በሀገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 101 እና በስራ ላይ ባለው የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 982/2008 እና በተወሰኑ አንቀጾቹን የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1146/2011 መሠረት ተሰጡትን ስልጣንና ኃላፊነቶች በውጤታማነት ሲያከናውን የኦዲት ሪፖርቶችን በተደራጀ መልክ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
ተጠያቂነት
ግልፅነት
መልካም አስተዳደር
ተጠያቂነት፣ ግልጽነት እና መልካም አስተዳደርን በመመሪያ የህዝብ ሀብት እንዲጠበቅ እና ለዜጎች የሚያገለግል ውጤታማ አገልግሎት እንዲደርስ እየተጋለጥን ነው።
80 ዓመታት
አገልግሎቶቻችን
የሚያስፈልጎትን መረጃ እናቀርባለን !
የሂሳብ እና ህጋዊነት ኦዲት
የመንግስት ተቋማት ዓመታዊ በጀታቸው፣ የክልል ድጎማዎች እና የለጋሾች ድጎማ ገንዘብ በገቢና ወጪ መዝገብ ትክክለኛ እንዲቀርብ የሚያረጋግጥ ምርመራ ነው። ከዚሁ ጋር የሚካሄዱ የህጋዊነት ኦዲቶች የህዝብና የመንግስት ሀብት በሕግ፣ በደንብና በመመሪያ እንዲተማመኑ ያረጋግጣሉ።
የክዋኔ ኦዲት
ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የተነደፈውን ዕቅድ፣ ሀብትና ሰው ኃይል በትክክል በመጠቀም ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያረጋግጡ የክዋኔ ምርመራዎች ናቸው።
የአካባቢ ኦዲት
የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት በበቂ ትኩረት እንዲፈጠሩ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች የተወሰኑ የልቀት መጠኖች እንዲጠበቁ የሚፈትሹ ኦዲቶች ናቸው።
የመረጃ ስርዓት ኦዲት
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተጠቃሚ የመረጃ ስርዓቶች ትክክለኛ መረጃ እንዲያመነጩ፣ ጥበቃ ስርዓታቸውም እንዲጠናከር የሚያረጋግጡ ኢቲ ኦዲቶች ናቸው።
ልዩ ኦዲት
በተለየ ጊዜ ለመግለጽ የሚያስፈልጉ የፋይናንስ፣ የሀብት አስተዳደር ወይም ትላልቅ ፕሮግራሞች አፈጻጸም ላይ ከመደበኛው ኦዲት ሂደት ውጪ የሚካሄዱ ጥናቶች ናቸው።
የስርዓተ ጾታ አካታችነት ኦዲት
ተቋማት በመዋቅራቸው፣ በስራ ሂደታቸው እና በተሳትፎ ደረጃቸው የስርዓተ ጾታን ጉዳዮች እንዲያካትቱ የሚፈትሹ ኦዲቶች ናቸው።
ሌሎች አገልግሎቶች
የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ የኦዲት ምክር አገልግሎት የኦዲት ችሎታ ግንባታ
ተጨማሪ ዜናዎች እና መረጃዎች
ተለይተው የቀረቡ የመገናኛ ሚዲያ ውጤቶች
ከዋና ኦዲተር ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
10/06/2025
አጋሮች እና ደንበኞች
ተጨማሪ መረጃ ያስፈልገዋታል?
ይጠይቁን ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን