News

የ2018 አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁና የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ተካሄደ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 አዲስ ዓመትን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁና የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ አዲሱ የ2018 ዓ.ም የስኬትና የበለጠ ተቋማዊ ውጤት የሚመዘገብበት አመት እንዲሆን ተመኝተው በ2017 ዓ.ም የተመዘገቡ ውጤታማ አፈጻጸሞችን ማጠናከርና የታዩ የአሠራር ክፍተቶችን በማረም ለበለጠ ስኬት መዘጋጀት እንደሚገባ አሳበዋል፡፡

መ/ቤቱ በተመሳሳይ አጋጣሚዎች በየጊዜው እያደረገ ያለውን የማዕድ መጋራት መርሀ ግብር ያስታወሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ የ2018 አዲስ አመትን አስመልክቶም ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የመ/ቤቱ ሠራተኞች የተለመደው የማዕድ መጋራት በመ/ቤቱ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አዲሱን የ2018 ዓ.ም መቀበያ በዓል አስመልክቶ በደረጃ VI እና ከዚያ በታች ባሉ የስራ መደቦች ለሚገኙ በጥቅሉ 96 የመ/ቤቱ ሠራተኞች ለበአል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው  የ5 ኪሎ የዳቦ ዱቄት፣ የ5 ኪሎ ስኳር እና የ5 ሊትር ዘይት ስጦታ ተበርክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *