የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦፖለቲካዊ ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ውይይት አካሄደዋል፡፡
ውይይቱን የከፈቱት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ እንደ ሃገር ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በጋራ መሻገር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር) ባጋሩት ሀሳብ በየጊዜው እየተለወጠ ያለውን የዓለም ጂኦፓለቲካ ቀድሞ በመረዳት የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ አካሄድና ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ የሚያስችል ዝግጁነት በሁሉም ዜጋ ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅማን ካላስከበረች እንደ ሀገር ልትቀጥል እንደማትችል አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ዶ/ር አብርሃም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በጥልቀት መገንዘብ ይገባልም ብለዋል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመካከላችን ልዩነት ሳንፈጥር ከአደናቃፊ አጀንዳዎች፣ አመለካከቶችና ሌሎች ፈተናዎች በመራቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በቀረበው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ምን ይጠበቃል በሚለው ጉዳይ ላይ ከበላይ አመራሮችና ሰራተኞች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

