News

ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ግኝቶቹን ለማስተካከል እያደረገ ያለውን አበረታች ጥረት ማጠናከር እንዳለበት ተገለጸ

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2015/2016 ኦዲት አመት የሂሳብ ኦዲት መሠረት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩነቨርሲቲ የ2015 በጀት አመት የፋይናንስ ሥርዓት ላይ የታዩ የአሠራር ጉድለቶች ላይ እየተወሰደ ያለው አበረታች ጥረት እንዲጠናከርና ቀሪ የአሠራር ክፍተቶችም እንዲስተካከሉ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተካሄደው ይፋዊ የውይይት መድረክ ተጠየቀ፡፡

ከህግና መመሪያ ውጭ በድምሩ ከብር 19.2 ሚሊዮን በላይ የጥቅማጥቅም ገንዘብ ክፍያ መፈጸሙ፣ ለተማሪዎች ምግብ ግብአት በሚል ከብር 20.3 ሚሊዮን በላይ በሚሆን ወጪ ከመመሪያ ውጪ የተፈጸመ የምግብ ግብአት ግዥን ጨምሮ ሌሎች መመሪያን ያልተከተሉ ግዥዎች መካሄዳቸው፣ በወቅቱ ያልተሰበሰበ ከ26.6 ሚሊዮን በላይ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩና ከዚህ ውስጥ ሰነድ ያልቀረበባቸው መኖራቸው፣ ከብር 3.6 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ ያለሂሳብ አርዕስቱ ተመዝግቦ መገኘቱ እና የፋይናንስ መመሪያን ያልተከተለ የበጀት አጠቃቀም መታየቱን ጨምሮ ከብር 266.9 ሚሊዮን በላይ በጀት በወቅቱ በስራ ላይ ሳይውል መገኘቱ እንዲሁም ከገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ውጪ የባንክ ሂሳብ ደብተር የመክፈትና የገቢና ወጪ ደረሰኝ የማሳተም አሠራሮች መተግበራቸው እና በሌላም በኩል በውሎ አበል አከፋፈል፣ በተከፋይና ተሰብሳቢ ሂሳብ ስርዓት እንዲሁም በንብረት አያያዝና አጠቃቀም ላይ የተከሰቱ መመሪያን ያልጠበቁ አሠራሮች በኦዲቱ መታየታቸው በመድረኩ ተጠቅሶ ግኝቶቹን ለማስተካከል እየተደረገ ያለው አበረታች ጥረትም መጠናከር ይገባዋል ተብሏል።

በግኝቶቹ ላይ ስለተወሰዱ እርምጃዎች ማብራሪያ እንዲሰጥ በይፋዊ ስብሰባው ለተገኙ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ዝርዝር ጥያቄዎች ቀርበው በአመራሮቹ የኦዲት ግኝቶቹን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ዝርዝር ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ኦዲቱን ተከትሎ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሰጡ የግኝት ማስተካከያ አስተያየቶች መሠረት እርምጃዎች መወሰዳቸውንና ቀሪዎችንም ለማስተካከል ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑንና በተለይም የግበአት ግዥና አቅርቦትን በተመለከተ የወጡ ህጎችና የአሠራር መመሪያዎችን ከፍላጎት አንጻር ለመተግበር ችግሮች እንዳሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገልፀዋል፡፡

ለኦዲት ግኝቶቹ የተወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተሰጡ ምላሾችንና በዩኒቨርሲቲው ተዘጋጅቶ የተላከውን የኦዲት ግኝት ማስተካከያ የድርጊት መርሀ ግብር መሠረት በማድረግ አስተየታቸውን የሰጡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠ በበኩላቸው ያለአግባብ ህግና መመሪያ በመተላለፍ የተፈጸሙ ድርጊቶች ተቀባይነት የሌላቸው በመሆናቸው መታረም እንዳለባቸው ጠቁመው የማስተካከያ እርምጃ ተወስዶባቸዋል የተባሉ ግኝቶችን ስለመስተካከላቸው በቀጣይ የክትትል ኦዲት የሚረጋገጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የኦዲቱን መነሻ ምክንያቶችና አላማ በማስቀደም በሰጡት አስተያየትም ዩኒቨርሲቲው ለኦዲት ግኝቶቹ የሰጠው ትኩረት በመልካም ጎኑ መሆኑን ገልጸው የሚሰሩ ስራዎች ተገቢ ህጎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ሊከተሉ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር ሳያውቅና ሳይፈቅድ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ሊዘጉ እንደሚገባና የጥቅማጥቅም ክፍያዎችና ግዢዎች የመንግስት ህጎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ተከትለው መፈጸም እንዳለባቸው በአስተያየታቸው ጨምረው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን በወቅቱ መሰብሰብ እንዲቻል ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግና የንብረት አያያዝና የነዳጅ አጠቃቀም ላይ ያሉ ችግሮችንም በአግባቡ ለመቆጣጠር የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቱን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በማጠቃለያ ሀሳባቸው ዩኒቨርስቲው በኦዲት ግኝቶቹ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አመስግነው ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችንና ችግሮችን ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ መፍትሔ ማግኘት እንደሚገባና በተለይ ለፋይናንስ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት እንደሚያስፈለግ ገልጸው አዲስ የግኝት ማስተካከያ የድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ እስከ ታህሣስ 20ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲቀርብ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

 

The University is requested to strengthen its Attempts of taking Corrective Measures on the Audit Findings

OFAG: 18 December 2024:- The public hearing held by the joint gathering of the Public Expenditure Administration and Controlling Affairs Standing Committee (PAC) and the Audit stakeholders requests the Ethiopian Police University to strengthen its encouraging corrective actions on the audit findings observed by the 2023/2024 audit year financial audit of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG).

According to the audit findings discussed on December 18,2024 at the Ethiopian Parliament, the audit disclosed several illegal and improper financial and property administration practices including Illegitimate purchases of inputs and properties, misuse of budgets, unlawful payments, and also unauthorized opening of the Bank accounts and preparing unofficial cash receipts without legal confirmation of the Ministry of Finance.

Next to fitting comments and discussions made by the standing committee and audit stakeholders on the audit findings, H.E. Mrs. Messeret Damtie, the Federal auditor General and H.E. Mr. Abera Tadesse, the Deputy Auditor General, OFAG Ethiopia confirmed that a number of financial and property administration systems of the University were found to be out of the legal financial and property management rules and regulations.

By appreciating the positive reactions of the university in admitting the audit findings and attempts of taking corrective measures, the OFAG executives finally recommended that the official rules, regulations, procedures and other legal principles should have to be practical in any institutional working systems as well.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *